La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ዜና መዋዕል 19:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሠላሳ ሁለ​ትም ሺህ ሰረ​ገ​ሎ​ችን የሞ​ዓ​ካን ንጉ​ሥና ሕዝ​ቡ​ንም ቀጠሩ፤ መጥ​ተ​ውም በሜ​ድባ ፊት ለፊት ሰፈሩ። የአ​ሞ​ንም ልጆች ከየ​ከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው ተሰ​ብ​ስ​በው ወደ ሰልፍ መጡ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ሠላሳ ሁለት ሺሕ ሠረገሎችንና ፈረሰኞችን እንዲሁም የመዓካን ንጉሥና ወታደሮች በገንዘብ ቀጠሩ፤ እነርሱም መጥተው በሜድባ አጠገብ ሲሰፍሩ፣ አሞናውያን ደግሞ ከየከተሞቻቸው ተሰብስበው ለጦርነት ወጡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሠላሳ ሁለትም ሺህ ሰረገሎች የመዓካንም ንጉሥ ሠራዊት ቀጠሩ፤ መጥተውም በሜድባ ፊት ለፊት ሰፈሩ። የአሞንም ልጆች ከየከተሞቻቸው ተሰብስበው ወደ ውግያ መጡ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የተከራዩአቸው ሠላሳ ሁለት ሺህ ሠረገሎችና የንጉሥ ማዕካ ሠራዊት መጥተው በሜዳባ አጠገብ ሰፈሩ፤ ዐሞናውያንም ከየከተሞቻቸው ወጥተው ለጦርነት ተዘጋጁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሠላሳ ሁለትም ሺህ ሠረገሎች የመዓካንም ንጉሥ ሕዝቡንም ቀጠሩ፤ መጥተውም በሜድባ ፊት ለፊት ሰፈሩ። የአሞንም ልጆች ከየከተሞቻቸው ተሰብስበው ወደ ሰልፍ መጡ።

Ver Capítulo



1 ዜና መዋዕል 19:7
12 Referencias Cruzadas  

የአ​ሞ​ንም ልጆች የዳ​ዊት ወገ​ኖች እንደ አፈሩ ባዩ ጊዜ፥ የአ​ሞን ልጆች ልከው ከቤ​ት​ሮ​ዖብ ሶር​ያ​ው​ያ​ንና ከሱባ ሶር​ያ​ው​ያን ሃያ ሺህ እግ​ረ​ኞ​ችን፥ ከአ​ማ​ሌቅ ንጉ​ሥም አንድ ሺህ ሰዎ​ችን፥ ከአ​ስ​ጦ​ብም ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎ​ችን ቀጠሩ።


ዳዊ​ትም ከእ​ርሱ አንድ ሺህ ሰረ​ገ​ሎች፥ ሰባት ሺህም ፈረ​ሰ​ኞች፥ ሃያ ሺህም እግ​ረ​ኞች ወሰደ፤ ዳዊ​ትም ለመቶ ሰረ​ገ​ሎች የሚ​ሆ​ኑ​ትን ብቻ አስ​ቀ​ርቶ የሰ​ረ​ገ​ሎ​ቹን ፈረ​ሶች ቋንጃ ቈረጠ።


ዳዊ​ትም ይህን በሰማ ጊዜ ኢዮ​አ​ብ​ንና የኀ​ያ​ላ​ኑን ሠራ​ዊት ሁሉ ላከ።


የኢ​ት​ዮ​ጵ​ያም ንጉሥ ዝሪ አንድ ሚሊ​ዮን ሰዎ​ችና ሦስት መቶ ሰረ​ገ​ሎች ይዞ ወጣ​ባ​ቸው፤ ወደ መሪ​ሳም መጣ።


ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም፥ የፈ​ር​ዖን ፈረ​ሶች፥ ሰረ​ገ​ሎ​ቹም፥ ፈረ​ሰ​ኞ​ቹም፥ ሠራ​ዊ​ቱም ሁሉ አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው፤ በባ​ሕሩ ዳር በብ​ኤ​ል​ሴ​ፎን ፊት ለፊት ባለው ገላጣ መን​ደር አን​ጻ​ርም ሰፍ​ረው አገ​ኙ​አ​ቸው።


ለራ​ሳ​ችሁ እዘኑ፤ ጣዖ​ታ​ች​ሁና መሠ​ዊ​ያ​ችሁ ያሉ​ባት ዲቦን ትጠ​ፋ​ለ​ችና፤ ወደ​ዚ​ያም ወጥ​ታ​ችሁ በሞ​ዓብ ናባው አል​ቅሱ፤ ወዮም በሉ፤ ራስ ሁሉ በራ ይሆ​ናል፤ ክን​ድም ሁሉ ይቈ​ረ​ጣል።


ዘራ​ቸ​ውም ከሐ​ሴ​ቦን እስከ ዴቦን ድረስ ጠፋ፤ ሴቶ​ቻ​ቸ​ውም ደግሞ በሞ​ዓብ ላይ እሳ​ትን አነ​ደዱ።”


ድን​በ​ራ​ቸ​ውም በአ​ር​ኖን ሸለቆ ዳር ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር ጀምሮ በሸ​ለ​ቆው መካ​ከል ያለ​ችው ከተማ፥ ሜሶ​ርም ሁሉ፥


በአ​ር​ኖን ሸለቆ ዳር ካለ​ችው ከአ​ሮ​ዔር፥ በሸ​ለ​ቆ​ውም መካ​ከል ካለ​ችው ከተማ ጀምሮ የሚ​ሶር ሜዳ ሁሉ እስከ ዲቦን ድረስ፥


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፤ ዘጠኝ መቶ የብ​ረት ሰረ​ገ​ሎች ነበ​ሩ​ትና፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ሃያ ዓመት እጅግ ያስ​ጨ​ን​ቃ​ቸው ነበር።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ለመ​ዋ​ጋት ተሰ​በ​ሰቡ፤ ሠላሳ ሺህ ሰረ​ገ​ሎች፥ ስድ​ስት ሺህም ፈረ​ሰ​ኞች፥ በባ​ሕ​ርም ዳር እን​ዳለ አሸዋ ብዙ ሕዝብ ነበሩ፤ ወጥ​ተ​ውም ከቤ​ቶ​ሮን በአ​ዜብ በኩል በማ​ኪ​ማስ ሰፈሩ።