Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 19:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የአ​ሞ​ንም ልጆች የዳ​ዊት ሰዎች እን​ዳ​ፈሩ ባዩ ጊዜ ሐናን የአ​ሞን ልጆች ንጉሥ ከሶ​ርያ መስ​ጴ​ጦ​ምያ፥ ከሶ​ርያ ሞዓካ፥ ከሱ​ባም ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና ፈረ​ሰ​ኞ​ችን ይቀ​ጥሩ ዘንድ አንድ ሺህ መክ​ሊት ብር ላከ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 አሞናውያን በዳዊት ዘንድ እንደ ተጠሉ ባወቁ ጊዜ፣ ሐኖንና አሞናውያን ከመስጴጦምያ፣ ከአራም መዓካና ከሱባ ሠረገሎችንና ፈረሰኞችን ለመከራየት አንድ ሺሕ መክሊት ብር ላኩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የአሞንም ልጆች በዳዊት ዘንድ እንደ ተጠሉ ባዩ ጊዜ ሐኖንና የአሞን ልጆች ከመስጴጦምያ፥ ከአራም-መዓካ፥ ከሱባ ሰረገሎችንና ፈረሰኞችን ለመቅጠር አንድ ሺህ መክሊት ብር ላኩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ዐሞናውያን በገዛ እጃቸው ዳዊትን ጠላት እንዳደረጉት ተገነዘቡ፤ ስለዚህም ሠላሳ አራት ሺህ ኪሎ የሚመዝን ብር ከፍለው ሠረገሎችንና ፈረሰኞችን ከላይኛው መስጴጦምያና የሶርያ ግዛቶች ከሆኑት ከማዕካና ከጾባ ተከራዩ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የአሞንም ልጆች በዳዊት ዘንድ እንደ ተጠሉ ባዩ ጊዜ ሐኖንና የአሞን ልጆች ከመስጴጦምያ፥ ከአራምመዓካ፥ ከሱባ ሠረገሎችንና ፈረሰኞችን ይቀጥሩ ዘንድ አንድ ሺህ መክሊት ብር ላኩ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 19:6
21 Referencias Cruzadas  

ያዕ​ቆ​ብም ስም​ዖ​ን​ንና ሌዊን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ክፉ አደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ብኝ፤ በዚች ሀገር በሚ​ኖሩ በከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንና በፌ​ር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያን ሰዎች ዘንድ አስ​ጠ​ላ​ች​ሁኝ። እኔ በቍ​ጥር ጥቂት ነኝ፤ እነ​ርሱ በእኔ ላይ ይሰ​በ​ሰ​ቡና ይወ​ጉ​ኛል፤ እኔና ቤቴም እን​ጠ​ፋ​ለን።”


የአ​ሞ​ንም ልጆች የዳ​ዊት ወገ​ኖች እንደ አፈሩ ባዩ ጊዜ፥ የአ​ሞን ልጆች ልከው ከቤ​ት​ሮ​ዖብ ሶር​ያ​ው​ያ​ንና ከሱባ ሶር​ያ​ው​ያን ሃያ ሺህ እግ​ረ​ኞ​ችን፥ ከአ​ማ​ሌቅ ንጉ​ሥም አንድ ሺህ ሰዎ​ችን፥ ከአ​ስ​ጦ​ብም ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎ​ችን ቀጠሩ።


ዳዊ​ትም ደግሞ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ግዛት ለማ​ስ​ፋ​ፋት በሄደ ጊዜ የሱ​ባን ንጉሥ የረ​አ​ብን ልጅ አድ​ር​አ​ዛ​ርን መታ።


ከደ​ማ​ስ​ቆም ሶር​ያ​ው​ያን የሱ​ባን ንጉሥ አድ​ር​አ​ዛ​ርን ሊረዱ በመጡ ጊዜ ዳዊት ከሶ​ር​ያ​ው​ያን ሃያ ሁለት ሺህ ሰዎ​ችን ገደለ።


የኤ​ማ​ትም ንጉሥ ቶዑ ዳዊት የሱ​ባን ንጉሥ አድ​ር​አ​ዛ​ርን፥ ጭፍ​ራ​ው​ንም ሁሉ እንደ መታ ሰማ።


ሰዎ​ችም ሄደው በሰ​ዎቹ ላይ የተ​ደ​ረ​ገ​ውን ለዳ​ዊት አስ​ታ​ወ​ቁት። ሰዎ​ቹም በብዙ አፍ​ረ​ዋ​ልና ይቀ​በ​ሏ​ቸው ዘንድ ሰዎ​ችን ላኩ፤ ንጉ​ሡም፥ “ጢማ​ችሁ እስ​ኪ​ያ​ድግ ድረስ በኢ​ያ​ሪኮ ተቀ​መጡ፥ ከዚ​ያም በኋላ ተመ​ለሱ” አለ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ አክ​ዓብ የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “ከእኔ ጋር ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ትሄ​ዳ​ለ​ህን?” አለው። እር​ሱም፥ “እኔ እንደ አንተ ነኝ፤ ሕዝ​ቤም ለሰ​ልፍ እንደ ሕዝ​ብህ ናቸው፤” ብሎ መለ​ሰ​ለት።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ከነ​ቢ​ያቱ አራት መቶ ሰዎ​ችን ሰብ​ስቦ፥ “ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ለሰ​ልፍ ልሂ​ድን? ወይስ ልቅር?” አላ​ቸው። እነ​ር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በን​ጉሥ እጅ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ታ​ልና ውጣ” አሉት።


የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉ​ሥና የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍጥ ልብሰ መን​ግ​ሥት ለብ​ሰው በሰ​ማ​ርያ በር መግ​ቢያ አጠ​ገብ በአ​ደ​ባ​ባይ በዙ​ፋ​ኖ​ቻ​ቸው ላይ ተቀ​ም​ጠው ነበር፤ ነቢ​ያ​ትም ሁሉ በፊ​ታ​ቸው ትን​ቢት ይና​ገሩ ነበር።


ደግ​ሞም ከእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ መቶ ሺህ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላን ሰዎ​ችን በመቶ መክ​ሊት ብር ቀጠረ።


ከአ​ሞ​ንም ልጆች ንጉሥ ጋር ተዋጋ፤ አሸ​ነ​ፋ​ቸ​ውም። በዚ​ያም ዓመት የአ​ሞን ልጆች መቶ መክ​ሊት ብር፥ ዐሥር ሺህም የቆ​ሮስ መስ​ፈ​ሪያ ስንዴ፥ ዐሥር ሺህም የቆ​ሮስ መስ​ፈ​ሪያ ገብስ ግብር ሰጡት። እን​ዲ​ሁም ደግሞ የአ​ሞን ልጆ​ችና ንጉ​ሣ​ቸው በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው፥ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውና በሦ​ስ​ተ​ኛው ዓመት ሰጡት።


በአ​ን​ደ​በቱ የማ​ይ​ሸ​ነ​ግል፥ በባ​ል​ን​ጀ​ራው ላይ ክፋ​ትን የማ​ያ​ደ​ርግ፥ ዘመ​ዶ​ቹ​ንም የማ​ያ​ሰ​ድብ።


የአ​ሕ​ዛብ አለ​ቆች ከአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ ጋር ተሰ​በ​ሰቡ፤ የም​ድር ኀይ​ለ​ኞች ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከፍ ከፍ ብለ​ዋ​ልና።


እነ​ር​ሱም፥ “በፈ​ር​ዖ​ንና በሹ​ሞቹ ፊት ሽታ​ች​ንን አግ​ም​ታ​ች​ሁ​ታ​ልና፥ ይገ​ድ​ለ​ንም ዘንድ ሰይ​ፍን በእጁ ሰጥ​ታ​ች​ሁ​ታ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ል​ከ​ታ​ችሁ፤ ይፍ​ረ​ድ​ባ​ች​ሁም” አሉ​አ​ቸው።


“እና​ን​ተን የሚ​ሰማ እኔን ይሰ​ማል፤ እና​ን​ተ​ንም እንቢ የሚል እኔን እንቢ ይላል፤ እኔ​ንም እንቢ የሚል የላ​ከ​ኝን እንቢ ይላል፤ እኔ​ንም የሚ​ሰማ የላ​ከ​ኝን ይሰ​ማል።”


እንግዲህ የማይቀበል ሰውን ያልተቀበለ አይደለም፤ መንፈስ ቅዱስን በእናንተ እንዲኖር የሰጠውን እግዚአብሔርን ነው እንጂ።


እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ሳኦል የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ጭፍራ እንደ መታ፥ ደግ​ሞም እስ​ራ​ኤል በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ዘንድ እንደ በረቱ ሰሙ፤ ሕዝ​ቡም ደን​ፍ​ተው ሳኦ​ልን ለመ​ከ​ተል ወደ ጌል​ጌላ ተሰ​በ​ሰቡ።


ሳኦ​ልም መን​ግ​ሥ​ቱን በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አጸና፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ካሉት ከጠ​ላ​ቶቹ ሁሉ ጋር፥ ከሞ​ዓ​ብም፥ ከአ​ሞ​ንም ልጆች፥ ከኤ​ዶ​ም​ያ​ስም፥ ከቢ​ዖ​ርም፥ ከሱ​ባም ነገ​ሥ​ታት፥ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ሁሉ ጋር ይዋጋ ነበር፤ በየ​ሄ​ደ​በ​ትም ሁሉ ድል ይነሣ ነበር።


አን​ኩ​ስም፥ “በሕ​ዝቡ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ እጅግ የተ​ጠላ ሆኖ​አል፤ ስለ​ዚ​ህም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ባሪያ ይሆ​ነ​ኛል” ብሎ ዳዊ​ትን አመ​ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos