መዝሙር 100:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምስጋና ወደ ደጆቹ፣ በውዳሴም ወደ አደባባዮቹ ግቡ፤ አመስግኑት፤ ስሙንም ባርኩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ደጆቹ በውዳሴ፥ ወደ አደባባዮቹም በምስጋና ግቡ፥ አመስግኑት፥ ስሙንም ባርኩ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እያመሰገናችሁ በመቅደሱ በሮች ግቡ፤ ምስጋናም በመስጠት ወደ አደባባዩ ሂዱ፤ አመስግኑት፤ ስሙንም አወድሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠማማ ልብም አልተከተለኝም፤ ክፉ ከእኔ በራቀ ጊዜ አላወቅሁም። |
ከዚያም ዳዊት ለመላው ጉባኤ፣ “አምላካችሁን እግዚአብሔርን ወድሱት” አላቸው። ስለዚህ የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ወደሱ፤ በእግዚአብሔር በንጉሡም ፊት ተደፍተው ሰገዱ።
እግዚአብሔር የተቤዣቸው ይመለሳሉ፤ በዝማሬ ወደ ጽዮን ይገባሉ፤ ዘላለማዊ ደስታን ይጐናጸፋሉ፤ ደስታና ሐሤት ይቀድማሉ፤ ሐዘንና ትካዜም ይሸሻሉ።