Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 96:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ለስሙ የሚገባውን ክብር ለእግዚአብሔር ስጡ፤ መባ ይዛችሁ በፊቱ ቅረቡ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ለስሙ የሚገባ ክብርን ለጌታ ስጡ፥ ቁርባን ያዙ፥ ወደ አደባባዮችም ግቡ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ለስሙ ተገቢ የሆነውን ክብር ለእግዚአብሔር ስጡ፤ ወደ መቅደሱም አደባባይ መባ ይዛችሁ ቅረቡ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 አቤቱ፥ ስለ ፍር​ድህ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት፥ የይ​ሁ​ዳም ሴቶች ልጆች ሐሤት አደ​ረጉ፤

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 96:8
21 Referencias Cruzadas  

በምስጋና ወደ ደጆቹ፣ በውዳሴም ወደ አደባባዮቹ ግቡ፤ አመስግኑት፤ ስሙንም ባርኩ፤


ለሕዝቡ መዳንን ሰደደ፤ ኪዳኑንም ለዘላለም አዘዘ፤ ስሙም የተቀደሰና የተፈራ ነው።


ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ይህን በመካከልሽ፣ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ አደርጋለሁ። ሃሌ ሉያ።


ለስሙ የሚገባ ክብር ለእግዚአብሔር ስጡ፤ በቅድስናው ግርማ ለእግዚአብሔር ስገዱ።


የጢሮስ ሴት ልጅ እጅ መንሻ ይዛ ትመጣለች፤ ሀብታሞችም ደጅ ይጠኑሻል።


የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት፣ ግብር ያመጡለታል፤ የዐረብና የሳባ ነገሥታት፣ እጅ መንሻ ያቀርባሉ።


የምድሪቱም ሕዝብ በሰንበታትና በወር መባቻ በዓላት በእግዚአብሔር ፊት በበሩ መግቢያ ላይ ይስገዱ።


“ከፀሓይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ፣ ስሜ በሕዝቦች መካከል የከበረ ይሆናል፤ በየስፍራውም ሁሉ ለስሜ ዕጣንና ንጹሕ ቍርባን ያቀርባሉ፤ ስሜ በሕዝቦች መካከል የከበረ ይሆናልና” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ሰውነታችሁን ቅዱስና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሕያው መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፤ ይህም እንደ ባለ አእምሮ የምታቀርቡት አምልኳችሁ ነው።


በእግዚአብሔር ወንጌል የክህነት ተግባር፣ ለአሕዛብ የክርስቶስ ኢየሱስ አገልጋይ ለመሆን ነው፤ ይኸውም አሕዛብ በመንፈስ ቅዱስ ተቀድሰው በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያለው መሥዋዕት እንዲሆኑ ነው።


ነገር ግን በእምነታችሁ መሥዋዕትና አገልግሎት ላይ እንደ መጠጥ ቍርባን ብፈስስ እንኳ ከሁላችሁ ጋራ ደስ ይለኛል፤ ሐሤትም አደርጋለሁ።


የሚያስፈልገኝን ሁሉ፣ ከሚያስፈልገኝም በላይ ተቀብያለሁ፤ የላካችሁትንም ስጦታ ከአፍሮዲጡ እጅ ተቀብዬ ተሞልቻለሁ፤ ይህም መዐዛው የጣፈጠ፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያለውና ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ነው።


ስለዚህ እኛም እርሱ የተሸከመውን ውርደት ተሸክመን ከሰፈር ውጭ ወደ እርሱ እንውጣ።


እናንተ ደግሞ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕት ታቀርቡ ዘንድ፣ ቅዱሳን ካህናት ለመሆን እንደ ሕያዋን ድንጋዮች መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ትሠራላችሁ።


ጌታ ሆይ፤ አንተን የማይፈራ፣ ስምህን የማያከብርስ ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህና። የጽድቅ ሥራህ ስለ ተገለጠ፣ ሕዝቦች ሁሉ ይመጣሉ፤ በፊትህም ይሰግዳሉ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos