የቀሩት ወደ አፌቅ ከተማ ሸሹ፤ በዚያም በሃያ ሰባቱ ሺሕ ላይ ቅጥሩ ተንዶ ወደቀባቸው። ቤን ሃዳድም ወደ ከተማዪቱ ሸሽቶ በመሄድ ወደ አንዲት እልፍኝ ገብቶ ተደበቀ።
ኢያሱ 19:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም የዑማን፣ የአፌቅንና የረአብን ምድር ይጨምራል። በዚህም ሃያ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው ይገኛሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዑማ፥ አፌቅ፥ ረዓብ ደግሞ ነበሩ፤ ሀያ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዑማ፥ አፌቅና ረሖብ ተብለው የሚጠሩትን ኻያ ሁለት ከተሞችና በዙሪያቸው የሚገኙ ታናናሽ ከተሞችን ይጨምራል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አርኮብ፥ አፌቅ፥ ረአውም ደግሞ ነበሩ፤ ሃያ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዑማ፥ አፌቅ፥ ረአብ ደግሞ ነበሩ፥ ሀያ ሁለት ከተሞችና መንደሮቻቸው። |
የቀሩት ወደ አፌቅ ከተማ ሸሹ፤ በዚያም በሃያ ሰባቱ ሺሕ ላይ ቅጥሩ ተንዶ ወደቀባቸው። ቤን ሃዳድም ወደ ከተማዪቱ ሸሽቶ በመሄድ ወደ አንዲት እልፍኝ ገብቶ ተደበቀ።
የሳሙኤልም ቃል ወደ እስራኤል ሁሉ ደረሰ። በዚያ ዘመን እስራኤላውያን ፍልስጥኤማውያንን ሊወጉ ወጡ፤ እስራኤላውያን በአቤንኤዘር፣ ፍልስጥኤማውያን ደግሞ በአፌቅ ሰፈሩ።