መዝሙር 9:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! በአንተ የሚተማመኑትን ሁሉ ስለማትተዋቸው ስምህን የሚያውቁ ሁሉ ይተማመኑብሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስምህን የሚያውቁ ይታመኑብሃል፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ የሚሹህን አትተዋቸውምና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ለተጨቆኑ መጠጊያ ይሁናቸው፥ በመከራም ጊዜ መሸሸጊያ ይሁንላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስምህን የሚወዱ ሁሉ በአንተ ይታመናሉ፥ አቤቱ፥ የሚሹህን አትተዋቸውምና። |
ዳዊት ሰሎሞንንም እንዲህ አለው፤ “ልጄ ሆይ፥ የአባትህን አምላክ እንድታውቅ፥ በሙሉ ልብና በፈቃደኛ አእምሮ እንድታገለግለው ዐደራ እልሃለሁ፤ እርሱ ሐሳባችንንና ምኞታችንን ሁሉ ያውቃል፤ ወደ እርሱ ብትቀርብ እርሱም ወደ አንተ ይቀርባል፤ ብትተወው ግን እርሱም ለዘለዓለም ይተውሃል፤
ለድኾች፥ ለመጻተኞችና ለችግረኞች በችግራቸው ጊዜ መጠጊያ ሆነህላቸዋል፤ ከዐውሎ ነፋስ የሚድኑበት ተገንና ከፀሐይ ቃጠሎ የሚጠለሉበት ጥላ ሆነህላቸዋል፤ የጨካኞች ምት የክረምት ወጀብ ግድግዳን እንደሚገፋ ያለ ነው።
ጨለማ በሆነ አገር በድብቅ አልተናገርኩም፤ የያዕቆብን ልጆች፦ ‘ቅርጽ በሌለው ቦታ ፈልጉኝ’ አላልኳቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር እውነቱን እናገራለሁ፤ ትክክል የሆነውንም ነገር እገልጣለሁ።
“ብርሃን በጨለማ ውስጥ ይብራ!” ብሎ የተናገረ እግዚአብሔር በክርስቶስ መልክ የሚያበራውን የእግዚአብሔርን ክብር የማወቅ ብርሃን እንዲሰጠን ብርሃኑን በልባችን ውስጥ እንዲበራ አደረገ።
ይህን መከራ የምቀበለውም በዚህ ምክንያት ነው፤ ነገር ግን ማንን እንዳመንኩ ስለማውቅ አላፍርበትም፤ የተሰጠኝንም ዐደራ እስከዚያ ቀን ድረስ መጠበቅ እንደምችል ተረድቼአለሁ።
የእግዚአብሔር ልጅ እንደ መጣና እውነተኛውን አምላክ እንድናውቅ አስተዋይ ልቡና እንደ ሰጠን እናውቃለን በልጁም በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከእርሱ ከእውነተኛው አምላክ ጋር ኅብረት አለን። ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛው አምላክና የዘለዓለም ሕይወት ነው።