የሐዘንዋም ጊዜ ሲፈጸም ዳዊት ሰው ልኮ ወደ ቤተ መንግሥት አስመጣት፤ ለእርሱም ሚስት ሆና ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ነገር ግን ዳዊት ያደረገው ነገር እግዚአብሔርን አሳዘነ።
መዝሙር 32:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኃጢአቴን ሳልናዘዝ በቀረሁ ጊዜ ቀኑን ሙሉ በመቃተቴ መላ ሰውነቴ ደከመ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀኑን ሙሉ ከመቃተቴ የተነሣ፣ ዝም ባልሁ ጊዜ፣ ዐጥንቶቼ ተበላሹ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁልጊዜ ከመጮኼ የተነሣ ዝም ባልሁ ጊዜ አጥንቶቼ ተበላሹ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አዲስ ምስጋናንም አመስግኑት፥ በእልልታም መልካም ዝማሬ ዘምሩለት፤ |
የሐዘንዋም ጊዜ ሲፈጸም ዳዊት ሰው ልኮ ወደ ቤተ መንግሥት አስመጣት፤ ለእርሱም ሚስት ሆና ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ነገር ግን ዳዊት ያደረገው ነገር እግዚአብሔርን አሳዘነ።
ልጆችሽ በወጥመድ ውስጥ እንደ ተያዘ ድኩላ በየመንገዱ አደባባይ ተዝለፍልፈው ወድቀዋል፤ በእነርሱም ላይ የአምላክሽ የእግዚአብሔር ተግሣጽና ቊጣ ወርዶባቸዋል።
ክፉ በሆነው ስግብግብነታቸው ምክንያት በእነርሱ ላይ ተቈጥቼ ነበር፤ እንዲሁም እነርሱን ቀጥቼ ተለይቼአቸው ነበር፤ እነርሱም ወደ ራሳቸው መንገድ ተመለሱ።
ሁላችንም እንደ ድብ በመጮኽ እንደ ርግብም ምርር ብለን በማልቅስ ፍትሕንና መዳንን ለማግኘት እንጠባበቃለን፤ እነርሱ ግን ከእኛ የራቁ ስለ ሆኑ አይገኙም።
የይሁዳ ሕዝብ ከጭንቀትና ከከባድ የባርነት ሥራ በኋላ ወደ ምርኮ ተወሰዱ፤ አሁን እነርሱ በሕዝቦች መካከል ሲኖሩ ዕረፍት አያገኙም፤ እነርሱ በጭንቀት ውስጥ እያሉ አሳዳጆቻቸው ደረሱባቸው።
በአልጋቸው ላይ ተጋድመው ይጮኻሉ እንጂ ከልባቸው ወደ እኔ አይጸልዩም፤ እህልና የወይን ጠጅ ለማግኘት ሰውነታቸውን ይተለትላሉ፤ በእኔም ላይ ያምፃሉ።