La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 27:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ብዙ ሠራዊት ቢከበኝም አልፈራም፤ ጠላቶቼ በጦርነት ቢያጠቁኝ እንኳ በእግዚአብሔር መተማመኔን አልተውም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሰራዊት ቢከብበኝ እንኳ፣ ልቤ አይፈራም፤ ጦርነት ቢነሣብኝ እንኳ፣ ልበ ሙሉ ነኝ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሠራዊትም ቢከብበኝ ልቤ አይፈራም፥ ጦርነትም ቢነሣብኝ በዚህ እተማመናለሁ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከኃ​ጥ​ኣን ጋር ነፍ​ሴን አት​ው​ሰ​ዳት፤ ክፋ​ትም በል​ባ​ቸው እያለ ከባ​ል​ን​ጀ​ራ​ቸው ጋር ሰላ​ምን ከሚ​ና​ገሩ ዐመፅ አድ​ራ​ጊ​ዎች ጋር አት​ጣ​ለኝ።

Ver Capítulo



መዝሙር 27:3
17 Referencias Cruzadas  

ያሐዚኤልም እንዲህ አለ፦ “ንጉሥ ሆይ! እናንተም የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ በሙሉ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ተስፋ አትቊረጡ፤ ይህንንም ታላቅ ሠራዊት ለመቋቋም አትፍሩ፤ ጦርነቱ የእግዚአብሔር ነው እንጂ የእናንተ አይደለም፤


አምላክህን መፍራትህ መተማመኛህ፥ ትክክለኛ መንገዶችህም፥ ተስፋህ አይደለምን?


እምነቱ ጽኑ ስለ ሆነና በእግዚአብሔርም ስለሚተማመን፥ ክፉ ወሬ አያስደነግጠውም።


በዙሪያዬ የከበቡኝን በብዙ ሺህ የሚቈጠሩትን ጠላቶቼን አልፈራቸውም።


ጌታ ሆይ! ተነሥ! አምላኬ ሆይ! መጥተህ አድነኝ! የጠላቶቼን መንጋጋ ስበር፤ ጥርሶቻቸውንም አድቅቅ።


የእግዚአብሔር ሰዎችም ይህን አይተው ይፈራሉ፤ እንዲህ እያሉ ይሳለቃሉ፤


ተቃዋሚዎቻችሁንም በምንም ነገር አትፍሩአቸው፤ ይህም ድፍረታችሁ ለእነርሱ የመጥፋታቸው ምልክት ሲሆን ለእናንተ ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ የመዳኛችሁ ምልክት ነው።


መልካም ነገር በማድረግ መከራን ብትቀበሉ እንኳ በረከትን ታገኛላችሁ፤ የሰዎችን ዛቻ አትፍሩ፤ አትጨነቁም።


ወደ ፊት የሚደርስብህን መከራ አትፍራ፤ እነሆ፥ እንድትፈተኑ ከእናንተ አንዳንዶቹን ዲያብሎስ ወደ እስር ቤት ያገባችኋል፤ ዐሥር ቀንም መከራ ትቀበላላችሁ፤ እስከ ሞት ድረስ ታማኝ ሁን፤ የሕይወት አክሊል እሰጥሃለሁ።


ከፍልስጥኤማውያን ጋር ይደረግ የነበረውም ጦርነት እንደገና አገረሸ፤ ሆኖም ዳዊት በእነርሱ ላይ ብርቱ አደጋ በመጣል ድል ስለ መታቸው ሸሽተው ሄዱ፤