መዝሙር 117:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ለእኛ ያለው ፍቅር ጽኑ ነው፤ ታማኝነቱም ዘለዓለማዊ ነው። እግዚአብሔር ይመስገን! አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምሕረቱ በእኛ ላይ ታላቅ ነውና፤ የእግዚአብሔርም ታማኝነት ለዘላለም ነው። ሃሌ ሉያ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍቅሩ በእኛ ላይ ጸንቶአልና፥ የጌታም እውነት ለዘለዓለም ትኖራለች። ሃሌ ሉያ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቸር እንደ ሆነ፥ ምሕረቱ ለዘለዓለም እንደ ሆነ፥ የእስራኤል ወገን ንገሩ። |
አምላክ ሆይ! አንተ አምላኬ ነህ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ስምህንም አመሰግናለሁ፤ አንተ እጅግ አስደናቂ የሆኑ ነገሮችን አድርገሃል፤ ከጥንት ጀምሮ ያቀድከውን ሁሉ፥ ፍጹምነት ባለው አስተማማኝ ሁኔታ አከናውነሃል።
ጥምቀቱን በሚያመለክት ውሃና ሞቱን በሚያመለክት ደም የመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ የመጣው በውሃ ብቻ ሳይሆን በውሃና በደም ነው። ይህም እውነት ስለ ሆነ ይህ ነገር እውነት መሆኑን መንፈስ ቅዱስ ይመሰክራል፤