መዝሙር 110:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር “በመልከ ጼዴቅ ሥርዓት አንተ ለዘለዓለም ካህን ትሆናለህ” ብሎ ማለ፤ መሐላውም የማይሻር ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እንደ መልከ ጼዴቅ ሥርዐት፤ አንተ ለዘላለም ካህን ነህ” ብሎ፣ እግዚአብሔር ምሏል፤ እርሱ ሐሳቡን አይለውጥም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እንደ መልከጼዴቅ ሥርዓት አንተ ለዘለዓለም ካህን ነህ ብሎ”፥ ጌታ ማለ፥ አይጸጸትምም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለጌትነቱ መታሰቢያን አደረገ፤ እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ ነው። |
የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ የሚመራ እርሱ ነው፤ የንጉሥነትን ክብር በመቀዳጀት በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ይገዛል፤ አንድ ካህን በዙፋኑ አጠገብ ይቆማል፤ ሁለቱም አብረው በስምምነትና በሰላም ይሠራሉ።’
እንግዲህ ለሕዝቡ ሕግ የተሰጠው በሌዊ ክህነት መሠረት ነው፤ በዚህ በሌዋውያን ክህነት ፍጹምነት ቢገኝ ኖሮ የአሮን የክህነት ሹመት ሳይሆን የመልከ ጼዴቅ የክህነት ሹመት ያለው ሌላ ካህን መምጣት ባላስፈለገም ነበር፤
ኢየሱስ ግን ካህን የሆነው በእግዚአብሔር መሐላ ነው፤ ይህም፦ “እግዚአብሔር ‘አንተ ለዘለዓለም ካህን ነህ’ ብሎ ምሎአል፤ አይለውጥም” ተብሎ በተነገረለት መሠረት ነው።
ሕግ የካህናት አለቆች አድርጎ የሚሾማቸው ደካሞች ሰዎችን ነው፤ ከሕግ በኋላ የመጣው የመሐላ ቃል ግን ለዘለዓለም ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔርን ልጅ ሾሞአል።
የኢየሱስ ክርስቶስን አባት እግዚአብሔርን እንድናገለግል ንጉሦችና ካህናት ላደረገን፥ ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ኀይል ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይሁን! አሜን።