ምሳሌ 22:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምግቡን ከድኾች ጋር ስለሚካፈል ለጋሥ ሰው የተባረከ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቸር ሰው ራሱ ይባረካል፤ ምግቡን ከድኾች ጋራ ይካፈላልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ርኅሩህ የተባረከ ይሆናል፥ ከእንጀራው ለድሀ ሰጥቶአልና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለድሃ የሚራራ እርሱ ይበላል እንጀራውን ለድሃ ሰጥቶአልና። ለሰጠው ሀብታምም የሚከፍል አይደለምና። መማለጃን የሰጠ ሰው ድል መንሣትንና ሞገስን ያገኛል፥ ነገር ግን የተቀበለውን ነፍስ ያጠፋል። |
‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ የተባረከ ነው’ የሚለውን የጌታ ኢየሱስን ቃል በማስታወስ፥ በእጃችን እየሠራን ደካሞችን መርዳት እንደሚገባን በብዙ መንገድ አሳይቻችኋለሁ።”
በመለሳለስና በቅምጥልነት በመካከልህ የምትኖር በትውልድዋ የምትመካና ከመለስለስዋ ብዛት እግሮችዋ መሬት ረግጠው የማያውቁ ዐቅፋው ከምትተኛው ባልዋና ከልጆችዋ ትሰስታለች።