ምሳሌ 12:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግ ሰው ከእግዚአብሔር ሞገስን ያገኛል፤ ክፉ ሐሳብ ያላቸውን ሰዎች ግን እርሱ ይፈርድባቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልካም ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ ያገኛል፤ ተንኰለኛውን ግን እግዚአብሔር ይፈርድበታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልካም ሰው ከጌታ ዘንድ ሞገስን ያገኛል፥ ተንኰለኛውን ሰው ግን ጌታ ይፈርድበታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተሻለ ሰው በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስን ያገኛል። ዐመፀኛ ሰው ግን ቸል ይባላል። |
የሕይወትን እስትንፋስ ለማስቀረትና የሞትን ቀን ለመለወጥ የሚችል ማንም የለም፤ ማንም ሰው ከጦር ሜዳ መሰናበት እንደማይችል ክፋትም ክፉ ሠሪዎችን አይለቃቸውም።