Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሮሜ 5:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 በጻድቅ ምትክ ሆኖ የሚሞት ሰው ማግኘት በጣም አስቸጋሪ ነው፤ ሆኖም በደግ ሰው ምትክ ለመሞት የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ለጻድቅ የሚሞት ሰው ማግኘት እጅጉን ያዳግታል፤ ለደግ ሰው ሲል ሊሞት የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ስለ ጻድቅ ሰው ሲል የሚሞት ሰው ማግኘት አስቸጋሪ ነው፤ ስለ መልካም ሰው ሲል ሊሞት የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ስለ ክፉ​ዎች በጭ​ንቅ ጊዜ ስንኳ ቢሆን ሊሞት የሚ​ደ​ፍር አይ​ገ​ኝም፤ ስለ ደጋጉ ግን ሊሞት የሚ​ጨ​ክን የሚ​ገኝ እን​ዳለ እንጃ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ስለ ጻድቅ የሚሞት በጭንቅ ይገኛልና፤ ስለ ቸር ሰው ግን ሊሞት እንኳ የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 5:7
11 Referencias Cruzadas  

ዘበኛውም “የመጀመሪያው ሰው የሚሮጠው ልክ እንደ ሳዶቅ ልጅ አሒማዓጽ ነው” አለ። ንጉሡም “እርሱ ጥሩ ሰው ነው፤ መልካም ወሬ ይዞ ይመጣል” አለ።


እነርሱም “አንተ ከእኛ ጋር መሄድ የለብህም፤ ጥቂቶቻችን ወደ ኋላ ተመልሰን ብንሄድ ወይም ግማሾቻችን ብንገደል ጠላት ምንም አይገደውም፤ አንተ ግን ከእኛ ዐሥሩን ሺህ ትበልጣለህ፤ ስለዚህ አንተ እዚሁ በከተማይቱ ውስጥ ቈይተህ አስፈላጊውን ርዳታ ብትልክልን ይሻላል” አሉት።


ሥራውን በቅንነት የሚመራ፥ ለጋሥ የሆነና ሳይሰስት የሚያበድር ኑሮው የተሳካለት ይሆናል።


የእዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአል፤ ጆሮአቸው ተደፍኖአል፤ ዐይናቸውም ተጨፍነዋል፤ እንዲህስ ባይሆን ኖሮ፥ በዐይናቸው ተመልክተው፥ በጆሮአቸውም ሰምተው፥ በልባቸውም አስተውለው፥ ወደ እኔ በተመለሱና በፈወስኳቸው ነበር።’


ሰው ሕይወቱን ስለ ወዳጆቹ አሳልፎ ከመስጠት የበለጠ ፍቅር የለውም።


እርሱ መንፈስ ቅዱስና እምነት የሞላበት ደግ ሰው ስለ ነበረ ቊጥራቸው ብዙ የሆኑ ሰዎች ወደ ጌታ ተመለሱ።


እነርሱ በእኔ ምትክ ለመሞት እንኳ የተዘጋጁ ነበሩ፤ በዚህም ዘወትር አመሰግናቸዋለሁ፤ እኔም ብቻ ሳልሆን ከአሕዛብነት ወደ ክርስትና የተመለሱ ምእመናን አብያተ ክርስቲያን ጭምር ያመሰግኑአቸዋል።


ገና ደካሞች ሆነን ሳለ እግዚአብሔር በወሰነው ጊዜ ክርስቶስ ስለ ኃጢአተኞች ሞተ።


ነገር ግን እኛ ኃጢአተኞች ሆነን ሳለ ክርስቶስ በእኛ ምትክ ሞቶአል፤ ይህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ፍቅር ምን ያኽል ታላቅ መሆኑን ያስረዳል።


ፍቅር ምን እንደ ሆነ የምናውቀው ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወቱን ለእኛ አሳልፎ ስለ ሰጠን ነው፤ እኛም ሕይወታችንን ስለ ወንድሞቻችን አሳልፈን መስጠት ይገባናል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos