ዘኍል 33:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያን በየነገዳቸው ተከፋፍለው በሙሴና በአሮን መሪነት ከግብጽ ከወጡ በኋላ በየጊዜው የሰፈሩባቸውን ቦታዎች የሚያስረዳው ታሪክ ይህ ነው፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን በየነገዳቸው ተከፋፍለው በሙሴና በአሮን መሪነት ከግብጽ ወጥተው፣ በጕዞ ላይ ሳሉ የሰፈሩባቸው ቦታዎች እነዚህ ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሙሴና በአሮን ልጅ እየተመሩ በየሠራዊታቸው ሆነው ከግብጽ በወጡ ጊዜ የእስራኤል ልጆች ያደረጉት ጉዞ ይህ ነበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሙሴና በአሮን እጅ ከሠራዊቶቻቸው ጋር ከግብፅ ከወጡ በኋላ የእስራኤል ልጆች የሰፈሩበት ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች ጕዞ ከሙሴና ከአሮን ልጅ በታች በጭፍሮቻቸው ከግብፅ በወጡ ጊዜ እንዲህ ነበረ። |
ስለዚህ ይህን በማድረግ ፈንታ ወደ ቀይ ባሕር በሚያመራው በረሓ፥ ዘወርዋራ በሆነ መንገድ መራቸው፤ እስራኤላውያንም ለጦርነት እንደ ተዘጋጁ ሆነው ከግብጽ ወጡ።
ያዕቆብና ቤተሰቡ ወደ ግብጽ ወርደው በዚያ ሲኖሩ ግብጻውያን የጭቈና ቀንበር ጫኑባቸው፤ የቀድሞ አባቶቻቸውም ርዳታ ለማግኘት ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እግዚአብሔር ሙሴንና አሮንን ላከላቸው፤ እነርሱም ከግብጽ መርተው በማውጣት በዚህች ምድር እንዲሰፍሩ አደረጉአቸው፤