እግዚአብሔር ጒዞአችንን እንዲያቃናልን፥ እኛንና ልጆቻችንን፥ እንዲሁም ንብረታችንን ሁሉ እንዲጠብቅልን በእርሱ ፊት ራሳችንን ዝቅ አድርገን እንለምነው ዘንድ በዚያው በአሀዋ ወንዝ አጠገብ ጾም ዐወጅኩ።
ዘኍል 29:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሰባተኛው ወር በገባ በዐሥረኛው ቀን ለማምለክ ትሰበሰባላችሁ፤ በዚያን ቀን ምግብ አትመገቡም፤ ሥራም አትሠሩም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘በዚሁ በሰባተኛው ወር በዐሥረኛውም ቀን የተቀደሰ ጉባኤ አድርጉ፤ ራሳችሁን አዋርዱ፤ ሥራም አትሥሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህም በሰባተኛው ወር በአሥረኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ፤ ራሳችሁንም አዋርዱ፤ ምንም ዓይነት ሥራ አትሥሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የዚህም ወር ዐሥረኛዋ ቀን ለእናንተ የተቀደሰች ትሁንላችሁ፤ ሰውነታችሁን አስጨንቁአት፤ ከሥራ ሁሉ ምንም አታድርጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህም ከሰባተኛው ወር በአሥረኛው ቀን የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ፤ ሰውነታችሁን አስጨንቁት፤ ከሥራ ሁሉ ምንም አታድርጉ። |
እግዚአብሔር ጒዞአችንን እንዲያቃናልን፥ እኛንና ልጆቻችንን፥ እንዲሁም ንብረታችንን ሁሉ እንዲጠብቅልን በእርሱ ፊት ራሳችንን ዝቅ አድርገን እንለምነው ዘንድ በዚያው በአሀዋ ወንዝ አጠገብ ጾም ዐወጅኩ።
“በዚያን ጊዜ በዳዊት ዘሮችና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ የርኅራኄና የጸሎት መንፈስ እሞላለሁ፤ ይህንንም የማደርገው እነርሱ ለአንድያ ልጅና ለበኲር ልጅ እንደሚለቀስ ለወጉት ምርር ብለው እንዲያለቅሱለት ነው።
የቤተ መቅደሱን ካህናትና ነቢያትን “እስከ አሁን ለብዙ ዓመቶች እንዳደረግነው በየአምስተኛው ወር በመጾም ስለ ቤተ መቅደሱ መፍረስ ማዘናችንን እንቀጥልን?” ብለው እንዲጠይቁ ነበር።
በጒዞአችን ላይ ብዙ ጊዜ በመባከኑና የጾም ጊዜ በማለፉ ምክንያት በዚህ ጊዜ በባሕር ላይ መጓዝ አደገኛ ስለ ነበር ጳውሎስ ለሰዎቹ እንዲህ ሲል አስጠነቀቃቸው፤