ዘኍል 14:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ! ይህን መልስ ስጣቸው፥ ‘በጠየቃችሁት ዐይነት እንደማደርግባችሁ ሕያው በሆነ ስሜ እምላለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እንዲህ በላቸው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ እኔ ሕያው ነኝ፤ ስትናገሩ የሰማኋችሁን እነዚያን ነገሮች አደርግባችኋለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህ በላቸው፦ ‘እኔ ሕያው ነኝና በጆሮዬ እንደ ተናገራችሁት እንዲሁ በእውነት አደርግባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህ በላቸው፦ እኔ ሕያው ነኝና በጆሮዬ እንደ ተናገራችሁት እንዲሁ በእውነት አደርግባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህ በላቸው፦ እኔ ሕያው ነኝና በጆሮዬ እንደ ተናገራችሁት እንዲሁ በእውነት አደርግባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ |
እኔ እግዚአብሔር በቀጥታ እናገራለሁ፤ የምናገረውም ቃል ሁሉ ይፈጸማል፤ ከእንግዲህ ወዲህም ከቶ አይዘገይም፤ እናንተ ዐመፀኞች ‘በእናንተ ላይ አመጣለሁ’ ብዬ በማስጠንቀቅ የተናገርኩትን ሁሉ በሕይወታችሁ ዘመን እንዲፈጸም አደርጋለሁ፤ ይህን የተናገርኩ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ነኝ።”
እስራኤላውያን ስለ ደረሰባቸው ችግር ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ ማጒረምረም ጀመሩ፤ እግዚአብሔርም የማጒረምረም ጩኸታቸውን ሰምቶ እጅግ በመቈጣት የሚባላ እሳት ላከባቸው፤ ያም እሳት ከሰፈሩ አንዱን ክፍል አወደመ።
ስለዚህ ለቀድሞ አባቶቻቸው ልሰጣቸው ቃል ወደገባሁላቸው ምድር በፍጹም አይገቡም፤ እኔን ከናቁኝ ሰዎች መካከል አንድ እንኳ ወደዚያች ምድር ከቶ አይገባም።
‘እኔ ለቀድሞ አባቶቻችሁ አወርሳታለሁ ብዬ የተስፋ ቃል ወደገባሁባት ወደዚያች ለም ምድር ከዚህ ክፉ ትውልድ መካከል አንዳችሁም አትገቡባትም።
ይህም የሆነው ቃዴስ በርኔን ትተን ከሄድን ከሠላሳ ስምንት ዓመት በኋላ መሆኑ ነው፤ እግዚአብሔር ስለ እነርሱ አስቀድሞ በመሐላ በተናገረው መሠረት ለጦርነት የደረሱ የዚያ ትውልድ ወንዶች ሁሉ አልቀው ነበር።