ንዕማን ግን ተቈጥቶ ወደ አገሩ ለመመለስ ተነሣ፤ እንዲህም እያለ ያጒረመርም ነበር፤ “እኔ እኮ ነቢዩ መጥቶ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ የቆዳው በሽታ ባረፈበት ገላዬ ላይ እጆቹን በመወዝወዝ ይፈውሰኛል ብዬ አስቤ ነበር!
ማርቆስ 5:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ትንሽዋ ልጄ በሞት አፋፍ ላይ ናት፤ እንድትድንና በሕይወት እንድትኖር እባክህ መጥተህ እጅህን ጫንባት!” ሲል አጥብቆ ለመነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ትንሿ ልጄ በሞት አፋፍ ላይ ናትና ድና በሕይወት እንድትኖር መጥተህ እጅህን ጫንባት” በማለት አጥብቆ ለመነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ትንሿ ልጄ በሞት አፋፍ ላይ ናትና እንድትድንና በሕይወት እንድትኖር መጥተህ እጅህን ጫንባት” በማለት አጥብቆ ለመነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ታናሽቱ ልጄ ልትሞት ቀርባለችና እንድትድንና በሕይወት እንድትኖር መጥተህ እጅህን ጫንባት፤” ብሎ አጥብቆ ለመነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታናሽቱ ልጄ ልትሞት ቀርባለችና እንድትድንና በሕይወት እንድትኖር መጥተህ እጅህን ጫንባት ብሎ አጥብቆ ለመነው። |
ንዕማን ግን ተቈጥቶ ወደ አገሩ ለመመለስ ተነሣ፤ እንዲህም እያለ ያጒረመርም ነበር፤ “እኔ እኮ ነቢዩ መጥቶ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ የቆዳው በሽታ ባረፈበት ገላዬ ላይ እጆቹን በመወዝወዝ ይፈውሰኛል ብዬ አስቤ ነበር!
እርሱም ማየት የተሳነውን ሰው እጅ ይዞ እየመራ ከመንደር ወደ ውጪ አወጣው፤ በሰውየውም ዐይኖች ላይ ምራቁን እንትፍ ብሎ እጁን ጫነበትና “አንዳች ነገር ታያለህን?” ሲል ጠየቀው።
ኢየሱስ ከምኲራብ ተነሥቶ ወደ ስምዖን ቤት ሄደ፤ እዚያም የስምዖን ዐማት በጣም አተኲሶአት ታማ ተኝታ ነበር፤ ስለዚህ እንዲያድናት ኢየሱስን ለመኑት።
ፀሐይ ስትጠልቅ ሰዎች በልዩ ልዩ ደዌ የተያዙባቸውን ሕመምተኞች ሁሉ ወደ ኢየሱስ አመጡ፤ እርሱም በእያንዳንዳቸው ላይ እጁን በመጫን ፈወሳቸው።
ኢየሱስ ወደ ከተማይቱ በር አጠገብ ሲደርስ እነሆ፥ ሰዎች ሬሳ ተሸክመው ከከተማይቱ ይወጡ ነበር፤ የሞተው ሰው ለእናቱ አንድ ነበር፤ እናቱም ባልዋ የሞተባት መበለት ነበረች፤ ከከተማይቱም ብዙ ሰዎች ተከትለዋት ነበር።
ስለዚህ ሐናንያ ወደዚያ ሄዶ እርሱ ወደ ነበረበትም ቤት ገባ፤ እጁንም በሳውል ላይ ጭኖ፥ “ወንድሜ ሳውል ሆይ! ወደዚህ ስትመጣ ሳለ በመንገድ የተገለጠልህ ጌታ ኢየሱስ እንደገና ማየት እንድትችልና መንፈስ ቅዱስም እንዲሞላብህ ወደ አንተ ልኮኛል” አለው።