ሰቈቃወ 3:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከችግር የተነሣ ሕይወት እንዲመረኝ አደረገ፤ በእሬትም አጠገበኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መራራ ሥር አበላኝ፤ ሐሞትም አጠገበኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምሬት ሞላብኝ በእሬትም አጠገበኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምሬትን አጠገበኝ፤ በሐሞትም አሰከረኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምሬት ሞላብኝ በእሬትም አጠገበኝ። |
“እንግዲህ እኔ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኢየሩሳሌም ነቢያት የምለው ይህ ነው፦ ‘በምድሪቱ ሁሉ ላይ የክሕደትን መንፈስ ስላሠራጩ፥ መራራ ቅጠል እንዲበሉና መርዝ እንዲጠጡ አደርጋቸዋለሁ።’ ”
ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “የእስራኤል አምላክ እኔ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ከማመጣው ጦርነት የተነሣ ሰክረው እስከሚያስመልሳቸውና ወድቀውም መነሣት እስኪሳናቸው ድረስ እንዲጠጡ የማዛቸው መሆኔን ለሕዝቡ ንገር፤
ይሁዳ ሆይ! ይህ ሁሉ የደረሰብሽ በአካሄድሽና በክፉ ሥራሽ ምክንያት ነው፤ ይህም ሁሉ የመረረ መከራ የመጣብሽ በኃጢአትሽ ምክንያት ስለ ሆነ ወደ ሰውነትሽ ዘልቆ ልብሽን አቊስሎታል።
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እኔ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የማደርገውን ነገር ልንገራችሁ፤ ይህ ሕዝብ ምግቡ መራራ መጠጡም የተመረዘ ውሃ እንዲሆንበት አደርጋለሁ።