ዮሐንስ 12:43 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም ያደረጉት ከእግዚአብሔር ከሚገኘው ክብር ይልቅ ከሰው የሚገኘውን ክብር ስለ ወደዱ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም የሆነው በእግዚአብሔር ከመመስገን ይልቅ በሰው መመስገንን ስለ ወደዱ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእግዚአብሔር ክብር ይልቅ የሰውን ክብር ወደዋልና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእግዚአብሔር ክብር ይልቅ የሰውን ክብር ወደዋልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእግዚአብሔር ክብር ይልቅ የሰውን ክብር ወደዋልና። |
ስለዚህ ለድኾች ምጽዋት በምትመጸውትበት ጊዜ፥ ግብዞች በየምኲራቡና በየመንገዱ እንደሚያደርጉት ለታይታ አታድርጉ፤ በእውነት እነግራችኋለሁ፥ እነርሱ ዋጋቸውን አስቀድመው አግኝተዋል።
እርሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ራሳችሁን በሰው ፊት ጻድቅ ታስመስላላችሁ፤ እግዚአብሔር ግን ልባችሁን ያውቃል፤ በሰው ፊት ክብር ያለው መስሎ የሚታይ፥ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ነው።”
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እኔ ራሴን ባከብር ክብሬ ዋጋ አይኖረውም እኔን የሚያከብረኝ አባቴ ነው፤ እርሱም ‘እናንተ አምላካችን’ የምትሉት ነው።
እውነተኛ አይሁዳዊ በውስጥ አይሁዳዊ የሆነ ነው፤ እውነተኛ መገረዝ በእግዚአብሔር መንፈስ የሚሆን የልብ መገረዝ ነው እንጂ በሕግ በተጻፈው መሠረት የሥጋ መገረዝ አይደለም። እንዲህ ዐይነቱም ሰው ምስጋናን የሚቀበለው ከእግዚአብሔር ነው እንጂ ከሰው አይደለም።
ስለዚህ ጊዜው ሳይደርስ፥ ጌታ ለፍርድ ከመምጣቱ በፊት በማንም ላይ አትፍረዱ፤ እርሱ በሚመጣበት ጊዜ በጨለማ የተሰወረውን ምሥጢር ወደ ብርሃን ያወጣዋል፤ በሰዎች ልብ የተደበቀውን ሐሳብ ይገልጠዋል፤ በዚያን ጊዜ እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ተገቢውን ምስጋና ያገኛል።
ነገር ግን ውበታችሁ በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ በከበረና በማይጠፋው ጌጥ በገርነትና በጭምትነት መንፈስ ያጌጠው፥ በልብ ተሰውሮ የሚገኘው፥ ውስጣዊ ሰውነት ይሁን።
ሳኦልም “በእርግጥ በደል ሠርቼአለሁ፤ ይሁን እንጂ ሌላው ቢቀር በሕዝቤ መሪዎችና በእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ፊት አክብረኝ፤ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር እሰግድ ዘንድ ከእኔ ጋር አብረህ ሂድ” ሲል ለመነው።
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘የአንተ ቤተሰብና የቀድሞ አባትህ ቤተሰብ ለዘለዓለም ያገለግሉኝ ዘንድ ቃል ገብቼ ነበር፤ አሁን ግን እንዲህ አይሆንም፤ የሚያከብሩኝን አከብራለሁ የሚንቁኝም ይናቃሉ።