ኢዮብ 9:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእርሱስ ጋር ማን ሊከራከር ይችላል? እርሱ አንድ ሺህ ጥያቄዎች ቢጠይቅ ከእነርሱ አንዱን እንኳ መመለስ የሚችል የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰው ከርሱ ጋራ ለመከራከር ቢፈልግ፣ ከሺሕ ጥያቄ አንዱን እንኳ መመለስ አይችልም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሱ ጋር መከራከር ቢፈልግ፥ ከሺህ ነገር አንዱን መመለስ አይችልም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእርሱ ጋር ይከራከር ዘንድ ቢወድድ፥ ከሺህ ነገር አንዱን መመለስ አይችልም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱ ጋር ይከራከር ዘንድ ቢወድድ፥ ከሺህ ነገር አንዱን መመለስ አይችልም። |
“ኢዮብ ሆይ! ለመሆኑ ሰው ሁሉን ከሚችል አምላክ ከእኔ ጋር ተከራክሮ ሊረታ የሚችል ይመስልሃልን? ከእኔ ከእግዚአብሔር ጋር የምትከራከር አንተ ስለ ሆንክ፥ እስቲ መልስ ስጥ።”
ከቊጥር በላይ የሆኑ ችግሮች ያስጨንቁኛል! በደሎቼ ስለ በዙ ማየት አልችልም፤ እነርሱም በቊጥር ከራስ ጠጒሮቼ ይበልጣሉ፤ ስለዚህ ልቤም እየከዳኝ ነው።