Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 9:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ታዲያ፥ እኔ ለእርሱ መልስ መስጠት እንዴት እችላለሁ? ከእርሱ ጋር ለመከራከርስ ምን ቃላት አገኛለሁ?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “ታዲያ፣ ከርሱ ጋራ እሟገት ዘንድ፣ ልከራከረውም ቃላት እመርጥ ዘንድ፣ እንዴት እችላለሁ?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ይልቁንስ እመልስለት ዘንድ፥ ቃሌንስ በፊቱ እመርጥ ዘንድ እኔ ማን ነኝ?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ቃሌን እን​ዴት ይሰ​ማ​ኛል? እን​ዴ​ትስ ይተ​ረ​ጕ​መ​ዋል?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ይልቁንስ እመልስለት ዘንድ፥ ቃሌንስ በፊቱ እመርጥ ዘንድ እኔ ማን ነኝ?

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 9:14
10 Referencias Cruzadas  

“በውኑ እግዚአብሔር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ ሰማያት፥ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ሊይዝህ አይችልም፤ እኔ የሠራሁት ይህ ቤተ መቅደስማ ምንኛ ያንስ?


አቤቱታዬን በፊቱ አሰማ ነበር፤ የመከላከያ መልሴንም በዝርዝር አቀርብ ነበር።


በዚያ ቅን ሰው ከእርሱ ጋር ይከራከራል፤ ዳኛዬ እግዚአብሔርም ለዘለዓለም ነጻ ያወጣኛል።


በስባሽና ትል የሆነው ሟች ሰውማ ምንኛ የባሰ ነው?”


“የምትችል ከሆነ ለንግግሬ መልስ ስጠኝ፤ ክርክሮችህን አመቻችተህ ቆመህ ተከራከረኝ።


አእምሮአችን ጨለማ በመሆኑ ጉዳያችንን ለማቅረብ ስለማንችል፥ ለእግዚአብሔር ምን እንደምለው ንገረን፤


ታዲያ፥ ምስጥ ሳይበላቸው የሚፈርሱ መሠረታቸው ዐፈር በሆነና ከሸክላ በተሠራ ቤት ውስጥ በሚኖሩትማ ላይ እንዴት ይተማመንባቸዋል?


ከእርሱስ ጋር ማን ሊከራከር ይችላል? እርሱ አንድ ሺህ ጥያቄዎች ቢጠይቅ ከእነርሱ አንዱን እንኳ መመለስ የሚችል የለም።


እርሱ እንደ እኔ ሰው ስላልሆነ፥ ወደ ፍርድ ሸንጎ ሄደን፥ እንፋረድ ልለው አልችልም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos