ስለዚህም ወዳጄ እንዲህ ይላል፦ “እናንተ የኢየሩሳሌምና የይሁዳ ሕዝብ ሆይ! በእኔና በወይን ተክል ቦታዬ መካከል ስላለው ነገር እስቲ ፍረዱ፤
ኤርምያስ 6:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “እናንተ ሕዝቦች ስሙ! በሕዝቤ ላይ የማደርገውንም ሁሉ አስተውሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ሕዝቦች ሆይ ስሙ፤ እናንተም ምስክሮች ምን እንደሚገጥማቸው አስተውሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሕዛብ ሆይ! ስለዚህ ስሙ፤ ማኅበር ሆይ! በእነርሱ ምን እንደሚደርስባቸው እወቁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሕዛብና የመንጋው ጠባቂዎች ሆይ፥ ስለዚህ ስሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሕዛብ ሆይ፥ ስለዚህ ስሙ፥ ማኅበር ሆይ፥ እነዚያ የሚያገኛቸውን እወቁ። |
ስለዚህም ወዳጄ እንዲህ ይላል፦ “እናንተ የኢየሩሳሌምና የይሁዳ ሕዝብ ሆይ! በእኔና በወይን ተክል ቦታዬ መካከል ስላለው ነገር እስቲ ፍረዱ፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቦች ሆይ! አድምጡኝ፤ በሩቅ ጠረፎችም ቃሌን ዐውጁ፤ እኔ ሕዝቤን በትኜ ነበር፤ አሁን ግን እሰበስባቸዋለሁ፤ እረኛ መንጋውን እንደሚጠብቅም እጠብቃቸዋለሁ።
እኔም፥ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! የኢየሩሳሌምን ሕዝብ ማታለል አይሆንብህምን? ‘ሰላም ይሆንላችኋል’ ብለሃቸው ነበር፤ እነሆ አሁን ሰይፍ በአንገታቸው ላይ ተቃጥቶአል” አልኩ።
ምድር ሆይ! ስሚ! እነርሱ ያስተማርኳቸውን ሥርዓት ስለ ተቃወሙ፤ ለሕጌም ስላልታዘዙ ስለ ክፉ ሐሳባቸው ሁሉ እቀጣቸው ዘንድ በሕዝቡ ላይ ጥፋትን አመጣለሁ።
ሕዝቤ ሆይ! የሞአብ ንጉሥ ባላቅ ምን እንደ ዐቀደብህና የቢዖር ልጅ በለዓም ምን እንደ መለሰለት አስታውስ፤ ከሺጢም ተነሥተህ ወደ ጌልጌላ በምትሄድበት ጊዜ በመንገድ ላይ የሆነውን ሁሉ አስታውስ፤ ይህን ሁሉ ብታስታውስ አንተን ለማዳን ያደረግኹትን ሁሉ ታውቃለህ።”