ዳዊትም ዐማሌቃዊውን “ይህን ጥፋት በራስህ ላይ ያመጣህ አንተው ራስህ ነህ፤ እግዚአብሔር መርጦ የቀባውን ንጉሥ ገድያለሁ ብለህ በተናገርክ ጊዜ በራስህ ላይ ፈርደሃል” አለው።
ሆሴዕ 12:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔርን እጅግ አስቈጡት፤ በበደላቸውም ይጠየቁበታል፤ ስሙንም ስለ ሰደቡ ይፈርድባቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤፍሬም ግን ክፉኛ አስቈጣው፤ ጌታውም የደም አፍሳሽነቱን በደል በላዩ ላይ ያደርግበታል፤ ስለ ንቀቱም የሚገባውን ይከፍለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም በነቢይ እጅ እስራኤልን ከግብጽ አወጣ፥ በነቢያትም እጅ ጠበቀው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም በነቢይ እስራኤልን ከግብፅ ምድር አወጣው፤ በነቢይም ጠበቀው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም በነቢይ እጅ እስራኤልን ከግብጽ አወጣ፥ በነቢያትም እጅ ጠበቀው። |
ዳዊትም ዐማሌቃዊውን “ይህን ጥፋት በራስህ ላይ ያመጣህ አንተው ራስህ ነህ፤ እግዚአብሔር መርጦ የቀባውን ንጉሥ ገድያለሁ ብለህ በተናገርክ ጊዜ በራስህ ላይ ፈርደሃል” አለው።
ገንዘቡን በአራጣ ቢያበድርና ከፍተኛ ወለድ ቢያስከፍል፥ ታዲያ እንዲህ ዐይነቱ ሰው በሕይወት ሊኖር ይችላልን? ከቶ በሕይወት ሊኖር አይችልም፤ ይህን ሁሉ አጸያፊ ነገር በማድረጉ በእርግጥ ይሞታል፤ ለሞቱም ተጠያቂው እርሱ ራሱ ይሆናል።
ከዚያ በኋላ በባሕር ጠረፍ ባሉት አገሮች ላይ አደጋ ጥሎ ከእነርሱ ብዙዎቹን ይይዛል፤ ነገር ግን አንድ የጦር መሪ ድል ስለሚነሣው የትዕቢቱ ፍጻሜ ይሆናል፤ በእርግጥም በትዕቢት የተናገረው ስድብ ሁሉ በእርሱ ላይ ይፈጸማል።
ከእኔ ርቀው ወደ ከንቱ አምልኮ ተመለሱ፤ ዓላማውን እንደሚስት እንደ ተበላሸ ቀስት ሆኑ፤ አለቆቻቸውም ክፉ ነገርን ከመናገራቸው የተነሣ በሰይፍ ተመተው ይሞታሉ፤ በግብጻውያንም ዘንድ መዘባበቻ ይሆናሉ።”
ይህ ሁሉ የሚደርስባችሁ የንጉሥ ዖምሪን ሥርዓት ስለ ጠበቃችሁና የንጉሥ አክዓብን አካሄድ ሁሉ ስለ ተከተላችሁ ነው፤ በእነርሱ ባህል ስለ ተመራችሁ አጠፋችኋለሁ፤ የከተማይቱን ነዋሪዎችም የሰው ሁሉ መሳቂያ አደርጋቸዋለሁ፤ በሕዝቤ ላይ የተሰነዘረውን ነቀፋ እንድትሸከሙ አደርጋችኋለሁ።”
እንደ አንተ ያለ ሌላ ነቢይ ከወንድሞቻቸው መካከል አስነሣላቸዋለሁ፤ እርሱ የሚናገረውን ቃል እሰጠዋለሁ፤ እኔም የማዘውን ሁሉ ለሕዝቡ ይነግራል፤
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘የአንተ ቤተሰብና የቀድሞ አባትህ ቤተሰብ ለዘለዓለም ያገለግሉኝ ዘንድ ቃል ገብቼ ነበር፤ አሁን ግን እንዲህ አይሆንም፤ የሚያከብሩኝን አከብራለሁ የሚንቁኝም ይናቃሉ።