ዘፍጥረት 41:41 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ! አሁን በመላው የግብጽ ምድር ላይ አስተዳዳሪ አድርጌሃለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም፣ ፈርዖን ዮሴፍን፣ “በመላዪቱ የግብጽ ምድር ላይ ኀላፊ አድርጌሃለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም፥ ፈርዖን ዮሴፍን “በመላዪቱ የግብጽ ምድር ላይ ኀላፊ አድርጌሃለሁ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈርዖንም ዮሴፍን፥ “በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ሾምሁህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርዖንም ዮሴፍን፦ በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ሾምሁህ አለው። |
ዮሴፍ የግብጽ ምድር አስተዳዳሪ በመሆኑ ከዓለም ዙሪያ ለሚመጡ ሰዎች ሁሉ እህል እንዲሸጥላቸው ያደርግ ነበር፤ ስለዚህ የዮሴፍ ወንድሞች ወደ እርሱ መጡና ግንባራቸው መሬት እስኪነካ ዝቅ ብለው እጅ ነሡት።
“ስለዚህ ወደዚህ የላከኝ ራሱ እግዚአብሔር እንጂ እናንተ አይደላችሁም፤ እግዚአብሔር ለፈርዖን እንደ መካሪ አባት፥ በቤት ንብረቱ ላይ ጌታና የመላው ግብጽ አገር ገዢ አደረገኝ።
አይሁዳዊው መርዶክዮስ በማዕርግ ደረጃ ከንጉሥ አርጤክስስ ቀጥሎ ሁለተኛ ነበር፤ እርሱም በወገኖቹ በአይሁድ ዘንድ በጣም የተከበረና የተወደደ ሰው ነበር፤ መርዶክዮስ ለወገኖቹና ለዘሮቻቸው በሰላም የመኖር ዋስትና ለማስገኘት በብርቱ የደከመ ሰው ነበር።
ከዚህ በኋላ ንጉሡ ዳንኤልን በታላቅ ክብር ቦታ አስቀመጠው፤ ብዙ ስጦታዎችንም ሰጠው፤ በባቢሎን ግዛትም ሁሉ ላይ የበላይ ገዢ አደረገው፤ በባቢሎንም ጠቢባን ሁሉ ላይ አለቃ አድርጎ ሾመው።
ዳንኤል ባለው ልዩ የሥራ ችሎታ ከሌሎቹ አገረ ገዢዎችና ባለ ሥልጣኖች በልጦ መገኘቱን በተግባር አስመሰከረ፤ ስለዚህ ንጉሡ በመንግሥቱ ሁሉ ላይ ኀላፊ አድርጎ ሊሾመው አሰበ።