ዘፍጥረት 30:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልያም “እንዴት የታደልኩ ነኝ!” ስትል ስሙን ጋድ ብላ ጠራችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልያም፣ “ምን ዐይነት መታደል ነው” አለች፤ ስሙንም ጋድ ብላ አወጣችለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልያም፦ ጉድ አለች፥ ስሙንም ጋድ ብላ ጠራችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልያም፥ “እኔም ራሴን ብፅዕት አሰኘሁ” ስትል ስሙን ጋድ ብላ ጠራችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልያም፦ ጉድ አለች ስሙንም ጋድ ብላ ጠራችው። |
“እኔን እግዚአብሔርን ትታችሁ የተቀደሰ ተራራዬን በመርሳት ‘መልካም አጋጣሚ’ ለተባለ ጣዖትም ማእድ ታዘጋጃላችሁ፤ ‘ዕድል ፈንታ’ ለተባለ ጣዖትም ዋንጫችሁን በተደባለቀ የወይን ጠጅ ትሞላላችሁ።