አንድ የእግዚአብሔር ነቢይ ወደ ንጉሥ አክዓብ ቀርቦ “እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ ‘ሶርያውያን፦ እግዚአብሔር የኮረብቶች አምላክ እንጂ የሜዳዎች አምላክ አይደለም ብለዋል፤ ከዚህም የተነሣ እኔ እጅግ ብዙ በሆነው ሠራዊታቸው ላይ ድልን አቀዳጅሃለሁ፤ አንተና ሕዝብህም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ’ ” አለው።
ዘፀአት 16:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እስራኤላውያን በእኔ ላይ ማጒረምረማቸውን ሰምቼአለሁ፤ ስለዚህ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘በዛሬው ምሽት ፀሐይ ከመጥለቅዋ በፊት ምግብ የሚሆናችሁን ሥጋ ታገኛላችሁ፤ በማለዳም የምትፈልጉትን ያኽል እንጀራ ታገኛላችሁ፤ በዚያን ጊዜም እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንኩ ታውቃላችሁ።’ ” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የእስራኤላውያንን ማጕረምረም ሰምቻለሁ፤ ይህን ንገራቸው፤ ‘ፀሓይ ከመጥለቋ በፊት ሥጋ ትበላላችሁ፤ ሲነጋም እንጀራ ትበላላችሁ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ መሆኔን ታውቃላችሁ።’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልን ልጆች ማጉረምረማቸውን ሰማሁ፦ እንዲህ በላቸው “ወደ ማታ ሥጋን ትበላላችሁ፥ ማለዳም እንጀራን ትጠግባላችሁ፤ እኔም ጌታ አምላካችሁ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የእስራኤልን ልጆች ማንጐራጐር ሰማሁ፦ ማታ ሥጋን ትበላላችሁ፤ ማለዳም እንጀራን ትጠግባላችሁ፤ እኔም እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ በላቸው።” |
አንድ የእግዚአብሔር ነቢይ ወደ ንጉሥ አክዓብ ቀርቦ “እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ ‘ሶርያውያን፦ እግዚአብሔር የኮረብቶች አምላክ እንጂ የሜዳዎች አምላክ አይደለም ብለዋል፤ ከዚህም የተነሣ እኔ እጅግ ብዙ በሆነው ሠራዊታቸው ላይ ድልን አቀዳጅሃለሁ፤ አንተና ሕዝብህም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ’ ” አለው።
እግዚአብሔርም “የቀድሞ አባቶቻቸው የአብርሃም፥ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር እንደ ተገለጥኩልህ ለእስራኤላውያን ማስረጃ ይሆን ዘንድ በዚህ ተጠቀም” አለው።
የእኔ ሕዝብ አደርጋችኋለሁ፤ እኔም አምላካችሁ እሆናለሁ፤ ከግብጽ ባርነትም ነጻ በማወጣችሁ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ መሆኔን ታውቃላችሁ፤
አሁን ግን በሚያደርገው ነገር የእግዚአብሔርን ማንነት በግድ ታውቃለህ፤ እነሆ፥ እኔ በዚህ በትር የአባይን ወንዝ ውሃ እመታለሁ፤ ውሃውም ወደ ደም ይለወጣል።
እነርሱ እኔ አምላካቸው እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር እንደ ሆንኩና እስራኤላውያን የእኔ ሕዝብ መሆናቸውን ያውቃሉ፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።
“እስራኤል ሆይ! በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንኩ ታውቃላችሁ፤ በተቀደሰው ተራራዬ በጽዮን ላይ እኖራለሁ፤ ኢየሩሳሌምም የተቀደሰች ከተማ ትሆናለች፤ ከእንግዲህ ወዲህ የባዕድ ወታደሮች አይወሩአትም።
እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ፤ እኔ ቅዱስ ስለ ሆንኩ እናንተም ራሳችሁን የተቀደሰ አድርጉ፤ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱትን ነፍሳት በመብላት ራሳችሁን አታርክሱ።
እነርሱንም ወደ እሳት እጨምራቸዋለሁ፤ ብርም በእሳት እንደሚጠራ አጠራቸዋለሁ፤ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፤ ከዚያን በኋላ ወደ እኔ ይጸልያሉ፤ እኔም እመልስላቸዋለሁ። እኔ ‘ሕዝቤ’ ብዬ እጠራቸዋለሁ፤ እነርሱም ‘እግዚአብሔር አምላካችን’ ብለው ይጠሩኛል።”
ከእስራኤላውያን ጋር የሚጓዙ የውጪ አገር ሰዎች ሥጋ ለመብላት የነበራቸው ፍላጎት ከፍተኛ ነበር፤ እስራኤላውያንም እንዲህ እያሉ ማልቀስ ጀመሩ፦ “የምንበላውን ሥጋ ከየት እናገኛለን!
“እነዚህ ክፉዎች የሆኑ ሰዎች በእኔ ላይ የሚያጒረመርሙት እስከ መቼ ነው? እነዚህ አጒረምራሚዎች እስራኤላውያን በእኔ ላይ ማጒረምረማቸውን ሰምቻለሁ።