Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 4:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እግዚአብሔርም “የቀድሞ አባቶቻቸው የአብርሃም፥ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር እንደ ተገለጥኩልህ ለእስራኤላውያን ማስረጃ ይሆን ዘንድ በዚህ ተጠቀም” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እግዚአብሔርም “ይህ የሆነው የአባቶቻቸው አምላክ፣ የአብርሃም አምላክ፣ የይሥሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር የተገለጠልህ መሆኑን እንዲያምኑ ነው” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 “ይህም የአባቶቻቸው አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅ አምላክ የያዕቆብም አምላክ፥ ጌታ እንደ ተገለጠልህ እንዲያምኑ ነው” አለው

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው አም​ላክ፥ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ፥ የይ​ስ​ሐ​ቅም አም​ላክ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ እንደ ታየህ ያም​ኑ​ሃል” አለው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 4:5
27 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለትና “ለዘርህ የምሰጠው ምድር ይህ ነው” አለው፤ ከዚህ በኋላ አብራም ለተገለጠለት አምላክ በዚያ ቦታ መሠዊያ ሠራ።


አብራም 99 ዓመት በሆነው ጊዜ እግዚአብሔር ተገለጠለትና “እኔ ኤልሻዳይ ሁሉን የምችል አምላክ ነኝ፤ ለእኔ በመታዘዝ ዘወትር ትክክል የሆነውን ነገር አድርግ፤


በመምሬ የወርካ ዛፎች አጠገብ እግዚአብሔር ለአብርሃም ተገለጠለት፤ የተገለጠለትም በዚህ ሁኔታ ነበር፤ ከዕለታት አንድ ቀን በቀትር ጊዜ አብርሃም በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ነበር፤


በዚያም እግዚአብሔር ለይስሐቅ ተገለጠለትና እንዲህ አለው፤ “ወደ ግብጽ አገር አትሂድ፤ እንድትኖርበት በምነግርህ በዚህ ምድር ተቀመጥ፤


እግዚአብሔርም በአጠገቡ ቆሞ እንዲህ አለው፤ “እኔ የአባትህ የአብርሃምና የይስሐቅ አምላክ እግዚአብሔር ነኝ፤ ለአንተና ለትውልድህ እንዲሆን ይህን የተኛህበትን ምድር እሰጥሃለሁ፤


ከዚህ በኋላ ዮሴፍን እንዲህ ሲል ባረከው፦ “አባቶቼ አብርሃምና ይስሐቅ መንገዱን በመከተል ያገለገሉትና እኔንም ሕይወቴን ሙሉ እስከ ዛሬ ድረስ እረኛ ሆኖ የጠበቀኝ አምላክ እነዚህን ልጆች ይባርክ!


ያዕቆብ ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “ሁሉን የሚችል አምላክ በከነዓን ምድር ሎዛ በምትባል ቦታ ተገለጠልኝ፤ ባረከኝም፤


ከቀትር በኋላ የሠርክ መሥዋዕት በሚቀርብበት ሰዓት ነቢዩ ኤልያስ ወደ መሠዊያው ቀርቦ እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “የአብርሃም፥ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! አንተ የእስራኤል አምላክ መሆንክን፥ እኔም የአንተ አገልጋይ መሆኔን፥ እኔም ይህን ሁሉ ያደረግኹት በቃልህ መሠረት መሆኑን አንተ ራስህ ግለጥ፤


ሰዎቹ በማግስቱ ጠዋት በማለዳ ተነሥተው ተቆዓ ተብሎ ከሚጠራ ስፍራ አጠገብ ወደሚገኘው በረሓማ አገር ሄዱ፤ ወደዚያ ለመሄድ ጒዞ በመጀመር ላይ ሳሉም ኢዮሣፍጥ እነርሱን “የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሰዎች ሆይ! በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ተማመኑ፤ እርሱም ብርታትን ይሰጣችኋል፤ የእግዚአብሔር ነቢያት የሚነግሩአችሁንም እመኑ፤ ይሳካላችኋልም” አላቸው።


እግዚአብሔርም ሙሴን “እኔ ግዙፍ በሆነ ደመና ወደ አንተ እመጣለሁ፤ ስለዚህም ሕዝቡ እኔ ከአንተ ጋር ስነጋገር በመስማት ከአሁን ጀምሮ አንተ የምትለውን ሁሉ ያምናሉ።” ሙሴም ሕዝቡ የሰጠውን መልስ ወደ እግዚአብሔር አቀረበ፤


እግዚአብሔርም እንደገና ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ በላቸው፦ የአባቶቻችሁ የአብርሃም፥ የይስሐቅ፥ የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር ወደ እናንተ ልኮኛል፤ ይህ የዘለዓለም ስሜ ነው፤ በዚህም ስም ከትውልድ እስከ ትውልድ እታወቃለሁ።


እንግዲህ ሂድና የእስራኤልን ሕዝብ አለቆች ሁሉ በአንድነት ሰብስብ፤ የቀድሞ አባቶቻቸው የአብርሃም የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ እኔ እግዚአብሔር የተገለጥኩልህ መሆኔንም ንገራቸው፤ ወደ እነርሱ ወርጄ ግብጻውያን በእነርሱ ላይ ያደረሱባቸውን ግፍና ጭቈና መመልከቴን ንገራቸው።


“ሕዝቤም አንተ የምትነግራቸውን ሁሉ ይሰማሉ፤ ከዚያም በኋላ ከእስራኤል ሕዝብ አለቆች ጋር ሆነህ ወደ ግብጽ ንጉሥ ሂድና ‘የዕብራውያን አምላክ እግዚአብሔር ተገልጦልናል፤ ስለዚህም ለአምላካችን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እናቀርብ ዘንድ የሦስት ቀን መንገድ ተጒዘን ወደ በረሓ እንድንሄድ ፍቀድልን’ ብላችሁ ንገሩት።


ሙሴም ሁኔታውን ለማየት በቀረበ ጊዜ እግዚአብሔር ተመለከተው፤ በቊጥቋጦውም መካከል ሆኖ “ሙሴ! ሙሴ!” ብሎ ጠራው። ሙሴም “እነሆ፥ አለሁ” አለ።


እኔ የቀድሞ አባቶችህ የአብርሃም፥ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ ነኝ፤” በዚህ ጊዜ ሙሴ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት ማየት ስለ ፈራ ፊቱን ሸፈነ።


ሙሴም እግዚአብሔርን “እስራኤላውያን ‘እግዚአብሔር አልተገለጠልህም’ ብለው ባያምኑኝና ቃሌን ባይሰሙ ምን እላቸዋለሁ?” አለው።


ሕዝቡም አመኑ፤ እግዚአብሔር ወደ እነርሱ መጥቶ እንደ ጐበኛቸውና የደረሰባቸውንም የግፍ ጭቈና ማየቱን በሰሙ ጊዜ ተንበርክከው ሰገዱ።


እግዚአብሔር ግን ሙሴን “እጅህን ዘርጋና ጅራቱን ይዘህ አንሣው” አለው። ሙሴም እጁን ዘርግቶ ጅራቱን በመያዝ ባነሣው ጊዜ እንደገና በትር ሆነ።


እንዲሁም የእስራኤል ራስ ሰማርያ ስትሆን፥ የሰማርያም ራስ ንጉሥ ፋቁሔ ነው። “ጽኑ እምነት ባይኖራችሁ እናንተም አትጸኑም።”


እኔ ለእነርሱ ከሩቅ ተገለጥኩላቸው፤ የእስራኤል ሕዝብ ሆይ፥ እነሆ እናንተን ለዘለዓለም ወደድኳችሁ፤ ዘለዓለማዊ ቸርነቴም ለእናንተ የጸና ይሆናል።


እናንተ እንድታምኑ እዚያ ባለመኖሬ ስለ እናንተ ደስ ብሎኛል፤ አሁን ግን ወደ እርሱ እንሂድ።”


ሁልጊዜም እንደምትሰማኝ ዐውቃለሁ፤ ነገር ግን ይህን ያልኩት፥ እዚህ የቆሙት ሰዎች አንተ እንደ ላክኸኝ እንዲያምኑ ብዬ ነው” አለ።


ከዚህ በኋላ ቶማስን፥ “ጣትህን ወዲህ አምጣና እጆቼን እይ፤ እጅህንም አምጣና በጐኔ ውስጥ አግባው፤ እመን እንጂ እምነተ ቢስ አትሁን” አለው።


ነገር ግን ኢየሱስ መሲሕ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን እንድታምኑና፥ አምናችሁም በእርሱ ስም የዘለዓለም ሕይወትን እንድታገኙ ይህ ተጽፎአል።


እኔ ግን ከዮሐንስ ምስክርነት የበለጠ ምስክር አለኝ፤ ምስክሬም አባቴ እንድሠራው የሰጠኝ ሥራ ነው፤ ይህም የምሠራው ሥራ፥ አብ እንደ ላከኝ ስለ እኔ ይመሰክራል።


እስጢፋኖስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ወንድሞቼና አባቶቼ ሆይ! እስቲ ስሙኝ! አባታችን አብርሃም በካራን ለመኖር ከመሄዱ በፊት ገና በመስጴጦምያ ሳለ የክብር አምላክ ተገለጠለትና


አሁን ግን የሚበልጠውን፥ በሰማይ ያለውን አገር ይናፍቃሉ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ከተማን ስላዘጋጀላቸው “አምላካችን” ብለው ቢጠሩት አያሳፍረውም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos