ይህም ከሆነ አሁን ያሉባትን በማርና በወተት የበለጸገችውን ለምለም ምድር የቀድሞ አባቶቻቸው እንዲወርሱ ባደረግሁ ጊዜ የሰጠኋቸውን የተስፋ ቃል እፈጽማለሁ።” እኔም “እሺ ጌታ ሆይ!” አልኩ።
ዘዳግም 27:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር በማርና በወተት የበለጸገችውን ምድር እንደሚሰጥህ ቃል በገባልህ መሠረት ምድሪቱን ለመያዝ በተሻገርህ ጊዜ የዚህን ሕግ ቃሎች በድንጋዮቹ ላይ ጻፍ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር በሰጠህ ተስፋ መሠረት፣ ማርና ወተት ወደምታፈስሰው አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን ስትሻገር፣ የዚህን ሕግ ቃላት ሁሉ ጻፍባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የአባቶችህ አምላክ ጌታ በሰጠህ ተስፋ መሠረት፥ ማርና ወተት ወደምታፈሰው ጌታ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን ስትሻገር፥ የዚህን ሕግ ቃላት ሁሉ ጻፍባቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር እንደ ተናገራችሁ፥ ወተትና ማር ወደምታፈስስ ምድር፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ትገቡ ዘንድ በተሻገራችሁ ጊዜ፥ የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ በድንጋዮች ላይ ጻፉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር ተስፋ እንደ ሰጠህ፥ ወተትና ማር ወደምታፈስስ ምድር፥ አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር ትገባ ዘንድ በተሻገርህ ጊዜ፥ የዚህን ሕግ ቃሎች ሁሉ ጻፍባቸው። |
ይህም ከሆነ አሁን ያሉባትን በማርና በወተት የበለጸገችውን ለምለም ምድር የቀድሞ አባቶቻቸው እንዲወርሱ ባደረግሁ ጊዜ የሰጠኋቸውን የተስፋ ቃል እፈጽማለሁ።” እኔም “እሺ ጌታ ሆይ!” አልኩ።
ነገር ግን ምድራቸውን ትወርሳላችሁ፤ በማርና በወተት የበለጸገችውን ምድር እንድትወርሱ እሰጣችኋለሁ፤ ከሌሎች ሕዝቦች እንድትለዩ ያደረግኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።
ለሙሴም እንዲህ ብለው ነገሩት፦ “ምድሪቱን አጥንተን በእርግጥም በማርና በወተት የበለጸገች አገር መሆንዋን ተረድተናል፤ ምድሪቱም የምታፈራው ፍሬ ዐይነት ይህ ነው፤
የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እነዚህን ሕግጋት አድምጡ! ታዘዙላቸውም! ይህን ብታደርጉ ለቀድሞ አባቶቻችሁ እግዚአብሔር በሰጠው ተስፋ መሠረት በማርና በወተት በበለጸገች በዚያች ለም ምድር ሁሉ ነገር በመልካም ሁኔታ ይከናወንላችኋል፤ ትበዛላችሁም።
ከግብጽ ምድር የወጡት ለወታደርነት ብቃት የነበራቸው ወንዶች የእግዚአብሔርን ቃል ባለመስማታቸው ሁሉም እስኪያልቁ ድረስ እስራኤላውያን በበረሓ ለአርባ ዓመት ተጓዙ። ለልጅ ልጆቻቸው ሊሰጥ ለቀድሞ አባቶቻቸው ቃል ገብቶ የነበረውን በማርና በወተት የበለጸገውን ምድር በምድረ በዳ ያለቁት ልጆቻቸው እንደማያዩት አረጋግጦ ነበር።