ዘዳግም 11:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ያደረጋቸውን እነዚህን ታላላቅ ነገሮች ሁሉ በዐይናችሁ ያያችሁ እናንተ ራሳችሁ ናችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእናንተ ዐይኖች ግን እግዚአብሔር ያደረጋቸውን ሥራዎች ሁሉ አይተዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእናንተ ዐይኖች ግን ጌታ ያደረጋቸውን ሥራዎች ሁሉ አይተዋል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ያደረጋቸውን ታላላቅ ሥራዎች ሁሉ ዐይኖቻችሁ አይተዋልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን እግዚአብሔር ያደረጋትን ታላቂቱን ሥራ ሁሉ ዓይኖቻችሁ አይተዋል። |
ከሮቤል ነገድ ወገን የኤልያብ ልጆች በሆኑት በዳታንና በአቤሮን ላይ ያደረገውን አስታውሱ፤ እስራኤላውያን ሁሉ በዐይናቸው እያዩ መሬት ተከፍታ እነርሱንና ቤተሰቦቻቸውን፥ ድንኳኖቻቸውንና ሕይወት ያለውና የእነርሱ የነበረውን ሁሉ ዋጠቻቸው።
በፔዖር ተራራ ላይ እግዚአብሔር ያደረገውን ሁሉ ራሳችሁ በዐይናችሁ አይታችኋል፤ ይኸውም በዚያ ተራራ ላይ ባዓል ተብሎ ለሚጠራው ጣዖት የሚሰግዱትን ሁሉ ደምስሶአል፤
በገዛ ዐይኖችህ ያየሃቸውን ታላላቅ መቅሠፍቶች፥ ተአምራትንና ድንቅ ሥራዎችን፥ እንዲሁም እግዚአብሔር አምላክህ አንተን ነጻ ያወጣበትን ታላቅ ኀይሉንና ሥልጣኑን አስታውስ፤ ግብጻውያንን ባጠፋበት ዐይነት ዛሬ አንተ የምትፈራቸውን እነዚህንም ሕዝቦች ሁሉ ያጠፋቸዋል።
ኢያሱ በሕይወት በነበረበት ጊዜ ሁሉ የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔርን አመለኩ፤ ከእርሱም ሞት በኋላ እግዚአብሔር ለእስራኤል ያደረገውን ድንቅ ነገር ሁሉ በዐይናቸው ያዩት ሽማግሌዎች እስከ ኖሩበት ዘመን ድረስ እርሱኑ በማምለክ ኖሩ።