በሠላሳኛው ዓመት፥ በአራተኛው ወር፥ ከወሩም በአምስተኛው ቀን በኬባር ወንዝ አጠገብ በአይሁድ ምርኮኞች መካከል ሳለሁ ሰማያት ተከፍተው የእግዚአብሔርን ራእይ አየሁ።
ዳንኤል 8:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብልጣሶር በነገሠ በሦስተኛው ዓመት እኔ ዳንኤል ከዚህ በፊት ካየሁት ሌላ ራእይ አየሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሥ ቤልሻዛር በነገሠ በሦስተኛው ዓመት፣ አስቀድሞ ከተገለጠልኝ ራእይ በኋላ እኔ ዳንኤል ሌላ ራእይ አየሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመጀመሪያ ከተገለጠልኝ ራእይ በኋላ፥ ንጉሡ ብልጣሶር በነገሠ በሦስተኛው ዓመት፥ ለእኔ ለዳንኤል ራእይ ተገለጠልኝ። |
በሠላሳኛው ዓመት፥ በአራተኛው ወር፥ ከወሩም በአምስተኛው ቀን በኬባር ወንዝ አጠገብ በአይሁድ ምርኮኞች መካከል ሳለሁ ሰማያት ተከፍተው የእግዚአብሔርን ራእይ አየሁ።
እግዚአብሔርም ለእነዚህ ለአራት ወጣቶች በማናቸውም ጥበብና ሥነ ጽሑፍ ዕውቀትና ማስተዋል ሰጣቸው፤ ዳንኤል ግን በተጨማሪ ራእይንና ሕልምን የመተርጐም ችሎታ ነበረው።
ነገር ግን ኀይሉ በገነነ ጊዜ መንግሥቱ ይፈርስና በአራት የዓለም ማእዘን ይከፈላል፤ በቦታውም የእርሱ ዘሮች ያልሆኑ ነገሥታት ይተካሉ፤ ይሁን እንጂ ከእነርሱ አንዱ እንኳ የእርሱን ያኽል ኀይል አይኖረውም፤ ይህም የሚሆነው ያ መንግሥት ፈርሶ እንደገና ለሌሎችም ስለሚከፋፈል ነው።
የባቢሎን ንጉሥ ብልጣሶር በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት በአልጋው ላይ ተኝቶ ሳለ፤ ዳንኤል ሕልምና ራእይ አየ፤ ከዚያም በኋላ ያየውን ሕልም ጻፈ።
የሕልሙም ትርጒም እዚህ ላይ ይፈጸማል፤ እኔም ዳንኤል እጅግ ሐሳቡ አስፈራኝ፤ በመደንገጥም ፊቴ ገረጣ፤ ይሁን እንጂ ሁሉንም ነገር በልቤ ሰውሬ ያዝኩ።
በነገሠም በመጀመሪያው ዓመት እኔ ዳንኤል ቅዱሳት መጻሕፍትን እየተመለከትኩ እግዚአብሔር ለነቢዩ ለኤርምያስ በነገረው መሠረት ኢየሩሳሌም ፍርስራሽ ሆና የምትቈይባት ዘመን ሰባ ዓመት መሆኑን ዐወቅሁ።