Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዳንኤል 8:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ንጉሥ ቤልሻዛር በነገሠ በሦስተኛው ዓመት፣ አስቀድሞ ከተገለጠልኝ ራእይ በኋላ እኔ ዳንኤል ሌላ ራእይ አየሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ብልጣሶር በነገሠ በሦስተኛው ዓመት እኔ ዳንኤል ከዚህ በፊት ካየሁት ሌላ ራእይ አየሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በመጀመሪያ ከተገለጠልኝ ራእይ በኋላ፥ ንጉሡ ብልጣሶር በነገሠ በሦስተኛው ዓመት፥ ለእኔ ለዳንኤል ራእይ ተገለጠልኝ።

Ver Capítulo Copiar




ዳንኤል 8:1
11 Referencias Cruzadas  

የባቢሎን ንጉሥ ቤልሻዛር በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት ዳንኤል በዐልጋው ላይ ተኝቶ ሳለ ሕልም ዐለመ፤ ራእይም አየ፤ የሕልሙንም ዋና ሐሳብ ጻፈው።


በኀይል እየገነነ ሳለም፣ መንግሥቱ ይፈርሳል፤ ወደ አራቱ የሰማይ ነፋሳትም ይከፋፈላል። መንግሥቱ ተወስዶ ለሌሎች ስለሚሰጥ፣ ለዘሩ አይተላለፍም፤ ኀይሉም እንደ መጀመሪያው አይሆንም።


ራእዩን ያየሁት እኔ ዳንኤል ብቻ ነበርሁ፤ ከእኔ ጋራ የነበሩት ሰዎች አላዩም፤ ነገር ግን ታላቅ ፍርሀት ስለ ወደቀባቸው ሸሽተው ተደበቁ።


በዚያ ጊዜ እኔ ዳንኤል ለሦስት ሳምንት አለቀስሁ፤


በዘመነ መንግሥቱ በመጀመሪያው ዓመት፣ እኔ ዳንኤል ለነቢዩ ለኤርምያስ በተሰጠው የእግዚአብሔር ቃል መሠረት፣ የኢየሩሳሌም መፈራረስ ሰባ ዓመት እንደሚቈይ ከቅዱሳት መጻሕፍት አስተዋልሁ።


እኔ ዳንኤል ራእዩን ስመለከትና ሳስተውል ሳለ፣ ሰውን የሚመስል ከፊት ለፊቴ ቆመ፤


“የነገሩ ፍጻሜ ይህ ነው፤ እኔም ዳንኤል በሐሳቤ እጅግ ተጨነቅሁ፤ መልኬም ተለዋወጠ፤ ይሁን እንጂ ነገሩን በልቤ ጠበቅሁት።”


“እኔ ዳንኤል በመንፈሴ ታወክሁ፤ ያየሁትም ራእይ እጅግ አስጨነቀኝ።


በሠላሳኛው ዓመት፣ በአራተኛው ወር፣ በዐምስተኛው ቀን፣ በኮቦር ወንዝ አጠገብ በምርኮኞች መካከል ሳለሁ፣ ሰማያት ተከፈቱ፤ እኔም የእግዚአብሔርን ራእይ አየሁ።


እግዚአብሔር ለእነዚህ አራት ወጣቶች በማንኛውም ሥነ ጽሑፍና ትምህርት ዕውቀትንና ማስተዋልን ሰጣቸው፤ ዳንኤልም ማንኛውንም ራእይና ሕልም የመረዳት ችሎታ ነበረው።


በራእዩም፣ በኤላም አውራጃ በሱሳ ግንብ ራሴን አየሁት፤ በራእዩም በኡባል ወንዝ አጠገብ ነበርሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios