የእነዚህ ሁሉ አገሮች አማልክት ከንጉሠ ነገሥታቶቻችን እጅ አገሮቻቸውን ለማዳን የቻሉበት ጊዜ አለን? ታዲያ እንግዲህ እናንተ ‘እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ያድናታል’ ብላችሁ የምታስቡት እንዴት ነው?”
ዳንኤል 3:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ የመለከት፥ የእንቢልታ፥ የመሰንቆ፥ የክራር፥ የበገና፥ የዋሽንትና፥ የሙዚቃም ሁሉ ድምፅ ስትሰሙ ላቆምኩት ምስል በመሬት ላይ ተደፍታችሁ ብትሰግዱ መልካም ነው፤ ባትሰግዱ ግን በሚነደው የእሳት ነበልባል ጒድጓድ ውስጥ ወዲያውኑ ትጣላላችሁ፤ ከእጄም የሚያድናችሁ አምላክ እንደሌለ ዕወቁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም ቢሆን የመለከቱንና የእንቢልታውን፣ የመሰንቆውንና የክራሩን፣ የበገናውንና የዋሽንቱን፣ የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ ስትሰሙ፣ እኔ ላቆምሁት የወርቅ ምስል ተደፍታችሁ ለመስገድ ዝግጁ ከሆናችሁ መልካም! ባትሰግዱለት ግን ወዲያውኑ ወደሚንበለበለው የእቶን እሳት ውስጥ ትጣላላችሁ፤ ታዲያ ከእጄ ሊያድናችሁ የሚችል አምላክ ማን ነው?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም የመለከቱንና የእንቢልታውን የመሰንቆውንና የክራሩን የበገናውንና የዋሽንቱን የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ተደፍታችሁ ላሠራሁት ምስል ብትሰግዱ መልካም ነው፥ ባትሰግዱ ግን በዚያ ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ትጣላላችሁ፥ ከእጄስ የሚያድናችሁ አምላክ ማን ነው? ብሎ ተናገራቸው። |
የእነዚህ ሁሉ አገሮች አማልክት ከንጉሠ ነገሥታቶቻችን እጅ አገሮቻቸውን ለማዳን የቻሉበት ጊዜ አለን? ታዲያ እንግዲህ እናንተ ‘እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ያድናታል’ ብላችሁ የምታስቡት እንዴት ነው?”
ንጉሡም “ለመሆኑ እግዚአብሔር ማን ነው? የእርሱንስ ትእዛዝ ሰምቼ እስራኤልን የምለቀው ለምንድን ነው? እኔ እግዚአብሔርን አላውቅም፤ እስራኤልንም አለቅም” አለ።
ዐይንህን በትዕቢት አቅንተህ፥ ድምፅህን ከፍ አድርገህ በመጮኽ የተዳፈርከውና የተሳደብከው ማንን ይመስልሃል? የእስራኤልን ቅዱስ አይደለምን?’
ንጉሡም ዳንኤልን “የአንተ አምላክ ከአማልክት ሁሉ የሚበልጥ አምላክ ነው፤ የነገሥታት ሁሉ ጌታ ነው፥ ምሥጢርንም ሁሉ መግለጥ የሚችል ነው፤ ከዚህም የተነሣ ይህን ታላቅ ምሥጢር ለመግለጥ ችለሃል” አለው።
ሕልሙን ልትነግሩኝ ባትችሉ ለሁላችሁም አንድ ዐይነት ቅጣት ተዘጋጅቶአል፤ ሁኔታዎች የሚለወጡ መስሎአችሁ የሐሰትና የተንኰል ቃል በመናገር ጊዜ ማራዘም ፈልጋችኋል፤ ስለዚህ ሕልሙን ብትነግሩኝ ፍቹም እንደማያስቸግራችሁ ዐውቃለሁ።”
ስለዚህ ዳንኤል ተይዞ መጥቶ ወደ አንበሶች ጒድጓድ እንዲጣል ንጉሡ አዘዘ፤ ዳንኤልንም “ሁልጊዜ በታማኝነት የምታገለግለው አምላክህ ያድንህ” አለው።
እዚያም በደረሰ ጊዜ ሐዘን በተሞላበት ድምፅ “የሕያው አምላክ አገልጋይ ዳንኤል ሆይ! ዘወትር በታማኝነት የምታገለግለው አምላክህ ከአንበሶቹ ሊያድንህ ችሎአልን?” ብሎ ተጣራ።
ሰዎች ወደ ፍርድ ሸንጎ ሲያቀርቡአችሁ የምትናገሩት ነገር በዚያን ሰዓት ስለሚሰጣችሁ፥ ‘እንዴት ወይም ምን እንናገራለን?’ ብላችሁ በማሰብ አትጨነቁ።
ሰዎች ይዘው ወደ ፍርድ ሲያቀርቡአችሁ፥ ‘ምን እንናገር ይሆን?’ በማለት አስቀድማችሁ አትጨነቁ፤ የሚናገረው መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ እናንተ አይደላችሁም። ስለዚህ በዚያን ሰዓት የሚሰጣችሁን ብቻ ተናገሩ።
“ሰዎች በየምኲራቡ ሲወስዱአችሁ፥ በገዢዎችና በባለሥልጣኖች ፊት ለፍርድ ሲያቀርቡአችሁ ‘ምን እንመልሳለን? እንዴትስ እንናገራለን?’ ብላችሁ አትጨነቁ።
ጴጥሮስና ዮሐንስ ግን እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፦ “ለእግዚአብሔር ከመታዘዝ ይልቅ ለእናንተ መታዘዝ በእግዚአብሔር ፊት ተገቢ ነውን? እስቲ እናንተ ራሳችሁ ፍረዱ።