2 ሳሙኤል 24:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮርዳኖስንም ተሻግረው በጋድ ውስጥ በሚገኘው ሸለቆ መካከል ባለችው በዓሮዔር ከተማ በስተ ደቡብ ሰፈሩ፤ ከዚያም ወደ ሰሜን አምርተው ወደ ያዕዜር ደረሱ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮርዳኖስን ከተሻገሩ በኋላ፣ በሸለቆው ውስጥ ካለችው ከተማ በስተ ደቡብ በምትገኘው በአሮዔር አጠገብ ሰፈሩ፤ ከዚያም በጋድ በኩል አድርገው ወደ ኢያዜር ሄዱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮርዳኖስን ከተሻገሩ በኋላ፥ በሸለቆው ውስጥ ካለችው ከተማ በስተ ደቡብ በምትገኘው በአሮዔር አጠገብ ሰፈሩ፤ ከዚያም በጋድ በኩል አድርገው ወደ ያእዜር ሄዱ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮርዳኖስንም ተሻገሩ፤ በጋድ ሸለቆ መካከል ባለችውም በኢያዜር ከተማ ቀኝ በኩል በአሮዔር ላይ ሰፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮርዳኖስንም ተሻገሩ፥ በጋድ ሸለቆ መካከል ባለችው በኢያዜር ከተማ ቀኝ በኩል በአሮዔር ላይ ሰፈሩ። |
ሙሴም ያዕዜርን የሚሰልሉ ሰዎች ላከ፤ እስራኤላውያንም ከተማይቱንና በዙሪያዋ ያሉትን ታናናሽ ከተሞች ያዙ፤ በዚያም ይኖሩ የነበሩትን አሞራውያን አባረሩ።
“ይህ እስራኤላውያን እንዲወርሱት እግዚአብሔር የረዳቸው የዐጣሮት፥ የዲቦን፥ የያዕዜር፥ የኒምራ፥ የሐሴቦን፥ የኤልዓሌ፥ የሲብማ፥ የነቦና የበዖን ከተሞች የሚገኙበት ምድር ለከብት ተስማሚ ነው፥ እኛ ደግሞ ብዙ ከብት አለን፤”
በአርኖን ሸለቆ ጠረፍ ከምትገኘው ከአሮዔርና በሸለቆው ከሚገኘው ከተማ ጀምሮ እስከ ገለዓድ ድረስ እኛን ሊቋቋመን የሚችል ከተማ አልነበረም፤ አምላካችን እግዚአብሔር ሁሉንም አሳልፎ ሰጠን።
ግዛታቸውም በአርኖን ሸለቆ ዳርቻ እስከሚገኘው እስከ ዓሮዔርና በዚያም ሸለቆ መካከል እስካለችው ከተማ አልፎ በሜደባ ዙሪያ ያለውን ሜዳማ አገር ሁሉ ያጠቃልላል፤
የእነርሱም ግዛት ያዕዜርንና በገለዓድ የሚገኙትን ከተሞች ሁሉ የዐሞንን ምድር እኩሌታ ጨምሮ ከራባ በስተምሥራቅ እስከምትገኘው እስከ ዓሮዔር ይደርሳል።
ግዛታቸውም ከአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ከሆነው ከዓሮዔር ተነሥቶ እንዲሁም በሸለቆው መካከል ካለው ከተማ ከሜዴባ ሜዳ እስከ ዲቦን ድረስ ይደርሳል።