አክዓብም “ግንባር ቀደም ሆኖ የሚዘምተው ማን ይሁን?” ሲል ጠየቀ። ነቢዩም “እግዚአብሔር ‘በአውራጃ አስተዳዳሪዎች የሚታዘዙ ወጣትነት ያላቸው ወታደሮች ግንባር ቀደም ሆነው ይዝመቱ’ ይላል” አለው፤ ንጉሡም “ጦርነቱን ማ ይጀምር” ሲል ጠየቀ። ነቢዩም “አንተ ራስህ ጀምር” አለው።
2 ነገሥት 9:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ንጉሥ ኢዮራም “ሠረገላዬን አዘጋጅልኝ” ሲል ትእዛዝ ሰጠ፤ ሠረገላውም ተዘጋጅቶለት እርሱና ንጉሥ አካዝያስ በየግል ሠረገላቸው እየጋለቡ ኢዩን ሊገናኙት ወጡ፤ እነርሱም ኢዩን ቀድሞ የናቡቴ ርስት በነበረው እርሻ ላይ አገኙት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮራምም፣ “ሠረገላዬን አዘጋጁ” ብሎ አዘዘ። ሠረገላው እንደ ተዘጋጀም፣ የእስራኤል ንጉሥ ኢዮራምና የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስ በየሠረገሎቻቸው ሆነው ኢዩን ለመገናኘት ሄዱ፤ የኢይዝራኤላዊው የናቡቴ ርስት በነበረው ዕርሻ ላይም ተገናኙት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ንጉሥ ኢዮራም “ሠረገላዬን አዘጋጅልኝ” ሲል ትእዛዝ ሰጠ፤ ሠረገላውም ተዘጋጅቶለት እርሱና ንጉሥ አካዝያስ በየግል ሠረገላቸው እየጋለቡ ኢዩን ሊገናኙት ወጡ፤ እነርሱም ኢዩን ቀድሞ የናቡቴ ርስት በነበረው እርሻ ላይ አገኙት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮራምም፥ “ሰረገላ አዘጋጁ” አለ፤ ሰረገላውንም አዘጋጁለት። የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮራምና የይሁዳ ንጉሥ አካዝያስ ሁለቱም በሰረገሎቻቸው ተቀምጠው ወጡ፤ ኢዩንም ሊገናኙት ሄዱ፤ በኢይዝራኤላዊውም በናቡቴ እርሻ ውስጥ አገኙት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮራምም “ሠረገላ አዘጋጁ፤” አለ፤ ሠረገላውንም አዘጋጁለት። የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮራም የይሁዳም ንጉሥ አካዝያስ በሠረገሎቻቸው ተቀምጠው ወጡ፤ ኢዩንም ሊገናኙት ሄዱ፤ በኢይዝራኤላዊው በናቡቴ እርሻ ውስጥ አገኙት። |
አክዓብም “ግንባር ቀደም ሆኖ የሚዘምተው ማን ይሁን?” ሲል ጠየቀ። ነቢዩም “እግዚአብሔር ‘በአውራጃ አስተዳዳሪዎች የሚታዘዙ ወጣትነት ያላቸው ወታደሮች ግንባር ቀደም ሆነው ይዝመቱ’ ይላል” አለው፤ ንጉሡም “ጦርነቱን ማ ይጀምር” ሲል ጠየቀ። ነቢዩም “አንተ ራስህ ጀምር” አለው።
አካዝያስ ኢዮራምን ሊጠይቅ የሄደው እግዚአብሔር ይህ ጒብኝት የአካዝያስ መጥፊያ እንዲሆን ስለ ፈቀደ ነው፤ አካዝያስ በዚያ በነበረበት ጊዜ እርሱና ኢዮራም የአክዓብን ሥርወ መንግሥት ለማጥፋት እግዚአብሔር የመረጠውን የኒምሺ ልጅ ኢዩን ለመቀበል ወጡ፤
ሙሴ ለኤዶም ንጉሥ እንዲህ ብለው እንዲነግሩት መልእክተኞችን ከቃዴስ ላከ፤ “ወንድምህ እስራኤል እንዲህ ይላል፦ በእኛ ላይ የደረሰውን ችግር ሁሉ ሰምተሃል፤