ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሰሎሞን ካህኑን አብያታርን እንዲህ አለው፤ “ወደ ትውልድ አገርህ ወደ ዐናቶት ሂድ፤ አንተ በሞት ልትቀጣ ይገባህ ነበር፤ ነገር ግን የልዑል እግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት በአባቴ በዳዊት ፊት ትሸከም ስለ ነበርክ ከእርሱም ጋር የመከራው ሁሉ ተካፋይ ስለ ነበርክ እኔ አሁን አልገድልህም
1 ሳሙኤል 30:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም የአቤሜሌክን ልጅ ካህኑን አብያታርን “ኤፉዱን አምጣልኝ” አለው፤ አብያታርም ኤፉዱን አመጣለት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ዳዊት የአቢሜሌክን ልጅ ካህኑን አብያታርን፣ “ኤፉዱን አምጣልኝ” አለው፤ አብያታርም አመጣለት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ዳዊት የአቤሜሌክን ልጅ ካህኑን አብያታርን፥ “ኤፉዱን አምጣልኝ” አለው፤ አብያታርም አመጣለት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም የአቤሜሌክን ልጅ ካህኑን አብያታርን፥ “ኤፉዱን አቅርብልኝ” አለው፤ አብያታርም ኤፉዱን ለዳዊት አቀረበለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም የአቢሜሌክን ልጅ ካህኑን አብያታርን፦ ኤፉዱን አቅርብልኝ አለው፥ አብያታርም ኤፋዱን ለዳዊት አቀረበለት። |
ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሰሎሞን ካህኑን አብያታርን እንዲህ አለው፤ “ወደ ትውልድ አገርህ ወደ ዐናቶት ሂድ፤ አንተ በሞት ልትቀጣ ይገባህ ነበር፤ ነገር ግን የልዑል እግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት በአባቴ በዳዊት ፊት ትሸከም ስለ ነበርክ ከእርሱም ጋር የመከራው ሁሉ ተካፋይ ስለ ነበርክ እኔ አሁን አልገድልህም
አብያታር የካህናት አለቃ በነበረበት ዘመን እርሱ ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ፥ ከካህናት በቀር ለሌሎች መብላት ያልተፈቀደውን፥ የተቀደሰውን የመባ ኅብስት በላ፤ ከእርሱም ጋር ለነበሩት ሰዎች ሰጣቸው።”
ስለዚህም እነርሱ “ሌላ የቀረ ይኖር ይሆን?” ሲሉ እግዚአብሔርን ጠየቁ። እግዚአብሔርም “ሳኦል እነሆ በዕቃ መካከል ተደብቆ ይገኛል” ሲል መለሰላቸው።
ሳኦል ከካህኑ ጋር በመነጋገር ላይ ሳለ፥ በፍልስጥኤማውያን ሰፈር የተነሣው ሁከትና ሽብር እየባሰበት ሄደ፤ ሳኦልም ካህኑን “እግዚአብሔርን ለመጠየቅ አሁን ጊዜ የለንም” አለው።