1 ጴጥሮስ 2:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቅዱስ መጽሐፍ “እነሆ! የተመረጠና ክቡር የሆነ የማእዘን ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ፤ በእርሱም የሚያምን አያፍርም” የሚል ቃል ተጽፎ ይገኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም በመጽሐፍ እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና፤ “እነሆ፤ የተመረጠና የከበረ የማእዘን ድንጋይ፣ በጽዮን አኖራለሁ፤ በርሱም የሚያምን ፈጽሞ አያፍርም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምክንያቱም በመጽሐፍ “እነሆ፥ የተመረጠና ክቡር የማእዘን ድንጋይ፥ በጽዮን አኖራለሁ፤ በእርሱም የሚያምን አያፍርም፤” ተብሎ ተጽፎአልና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመጽሐፍ “እነሆ የተመረጠና የከበረን የማዕዘን ራስ ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ፤ በእርሱም የሚያምን አያፍርም፤” ተብሎ ተጽፎአልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመጽሐፍ፦ እነሆ፥ የተመረጠና የከበረን የማዕዘን ራስ ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ በእርሱም የሚያምን አያፍርም ተብሎ ተጽፎአልና። |
አንድ ጊዜ በራእይ ለታማኝ አገልጋይህ እንዲህ ብለህ ተናግረሃል፤ “አንዱን ታላቅ ጀግና ረድቼአለሁ፤ ከሕዝቤ መካከል መርጬ ዘውድን አቀዳጅቼዋለሁ።
ስለዚህም ጌታ እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ “እነሆ፥ የጸና የመሠረት ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ፤ እርሱም የተመሰከረለት፥ የከበረ የማእዘን ድንጋይ ነው፤ በእርሱም የሚያምን ሁሉ አይናወጥም።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ የምደግፈው የመረጥኩትና በእርሱም ደስ የሚለኝ አገልጋዬ ይህ ነው፤ መንፈሴ በእርሱ እንዲያድርበት አደርጋለሁ፤ እርሱ ለሕዝቦች ሁሉ ትክክለኛ ፍርድን ያመጣል።
ኀፍረትም ሆነ ውርደት ስለማይደርስብሽ አትፍሪ፤ በወጣትነትሽ ጊዜ የደረሰብሽን ኀፍረት ትረሺአለሽ፤ ባልዋ እንደ ሞተባት ሴት ብቸኛ ሆነሽ ያሳለፍሽውን የስድብ ዘመን አታስታውሺም።
“እነሆ! የመረጥኩት አገልጋዬ ይህ ነው! እርሱ እኔ የምወደውና የምደሰትበት ነው፤ መንፈሴን በእርሱ ላይ አደርጋለሁ፤ እርሱም ቅን ፍርድን ለሕዝቦች ያውጃል።
ኢየሱስ ግን ወደ እነርሱ ተመልክቶ እንዲህ አለ፤ “ታዲያ፥ ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ የማእዘን ራስ ሆነ’ ተብሎ የተጻፈው ምንን ያመለክታል?
ሕዝቡ ቆሞ ይመለከት ነበር፤ የአይሁድ አለቆችም “ሌሎችንስ አዳነ እንግዲህ እርሱ የተመረጠው የእግዚአብሔር መሲሕ ከሆነ እስቲ ራሱን ያድን!” እያሉ ያፌዙበት ነበር።
“ወንድሞች ሆይ፥ ኢየሱስን ለያዙት ሰዎች መሪ ስለ ሆናቸው ስለ ይሁዳ፥ መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ በዳዊት አፍ የተናገረው የቅዱስ መጽሐፍ ቃል መፈጸም ነበረበት።
ቅዱስ መጽሐፍ በሙሉ በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት የተጻፈ ነው፤ እርሱ እውነትን ለማስተማር፥ የተሳሳቱትን ለመገሠጽ፥ ስሕተትን ለማረምና ለትክክለኛ ኑሮ የሚበጀውን መመሪያ ለመስጠት ይጠቅማል።
ስለዚህ ሕያው ድንጋይ ወደ ሆነው ወደ ጌታ ኢየሱስ ቅረቡ፤ ይህ ድንጋይ ሰዎች ንቀው የተዉት፥ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን የተመረጠና ክቡር ዋጋ ያለው ነው።
ደግሞም፥ “እነሆ! ሰዎችን የሚያሰናክል ድንጋይ፤ እነሆ! ሰዎችን አደናቅፎ የሚጥል አለት” ይላል። እነርሱ ቃሉን ባለማመናቸው ይሰናከላሉ፤ አስቀድመውም ለዚህ የተመደቡ ናቸው።
ከሁሉ በፊት ማስተዋል የሚገባችሁ በቅዱስ መጽሐፍ የሚገኘውን ማንኛውንም ትንቢት ማንም ሰው በራሱ ግላዊ አስተሳሰብ ሊተረጒመው የማይችል መሆኑን ነው።
እርሱ ስለዚህ ጉዳይ በመልእክቶቹ ሁሉ በዚሁ ዐይነት ጽፎአል፤ በመልእክቶቹ ውስጥ አንዳንድ ለመረዳት የሚያስቸግሩ ነገሮች አሉ። ዕውቀት የጐደላቸውና ወላዋዮች ሌሎችን ቅዱሳት መጻሕፍት እንደሚያጣምሙ እነዚህንም ነገሮች ያጣምማሉ፤ ይህንንም የሚያደርጉት ለጥፋታቸው ነው።