መዝሙር 36:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመዘምራን አለቃ፥ የጌታ ባርያ የዳዊት መዝሙር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉውን ሰው፣ በደል በልቡ ታናግረዋለች፤ ፈሪሀ እግዚአብሔር፣ በዐይኖቹ ፊት የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉ ሰው ሁልጊዜ በልቡ ክፋትን ያስባል፤ እግዚአብሔርን ከቶ አይፈራም፤ አያከብረውምም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በክፉዎች ላይ አትቅና፥ ዐመፃንም በሚያደርጉ ላይ አትቅና፤ |
የእግዚአብሔር ባርያና የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ፥ በእግዚአብሔርም የተመረጡት ያላቸውን እምነትና እግዚአብሔርን በመምሰል ላይ የተመሠረተውን የእውነት እውቀት ለማስፋፋት፥
የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይና ሐዋርያ ከሆነው ከስምዖን ጴጥሮስ፥ በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ ካገኘነው ጋር አቻ የሆነ ክቡር እምነትን ላገኙ፤
በቶሎ ሊሆን የሚገባውን ነገር ለአገልጋዮቹ ያሳይ ዘንድ እግዚአብሔር የሰጠው የኢየሱስ ክርስቶስ ራእይ ይህ ነው፤ መልአኩንም ልኮ ራእዩን ለአገልጋዩ ለዮሐንስ ገለጠ፤
ከዚያም ሳኦል ባለሟሎቹን፥ “ለዳዊት፥ ‘እነሆ፤ ንጉሡ በአንተ ደስ ብሎታል፤ ባለሟሎቹም ሁሉ ይወዱሃል፤ ስለዚህ ዐማቹ ሁንለት’ ብላችሁ በምስጢር ንገሩት” ብሎ አዘዛቸው።