ምሳሌ 17:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመልካም ፋንታ ክፉን የሚመልስ፥ ክፉ ነገር ከቤቱ አትርቅም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በበጎ ፈንታ ክፉ የሚመልስ ሰው፣ ክፉ ነገር ከቤቱ አይርቅም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግ ነገር ተደርጎለት ክፉ ነገር የሚመልስ ክፉ ነገር ዘወትር ከቤቱ አይለይም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመልካም ፋንታ ክፉን የሚመልስ፥ ክፉ ነገር ከቤቱ አይርቅም። |
ዮናታን ለአባቱ ለሳኦል፥ ስለ ዳዊት እንዲህ ሲል መልካም ነገር ተናገረ፥ “ንጉሥ በአገልጋዩ በዳዊት ላይ ክፉ ነገር አያድርግ፤ እርሱ አልበደለህም፤ ያደረገውም ነገር በእጅጉ ጠቅሞሃል።
ዳዊትም እንዲህ ብሎ ነበር፤ “ምንም ነገር እንዳይጠፋበት የዚህን ሰው ሀብት በምድረ በዳ ያን ያህል መጠበቄ ለካ በከንቱ ኖሯል፤ ደግ በሠራሁ ይኸው ክፉ መለሰልኝ።