Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ሳሙኤል 25:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ዳዊትም እንዲህ ብሎ ነበር፤ “ምንም ነገር እንዳይጠፋበት የዚህን ሰው ሀብት በምድረ በዳ ያን ያህል መጠበቄ ለካ በከንቱ ኖሯል፤ ደግ በሠራሁ ይኸው ክፉ መለሰልኝ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ዳዊትም እንዲህ ብሎ ነበር፤ “ምንም ነገር እንዳይጠፋበት የዚህን ሰው ሀብት በምድረ በዳ ያን ያህል መጠበቄ ለካ በከንቱ ኖሯል፤ ደግ በሠራሁ ይኸው ክፉ መለሰልኝ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ዳዊትም በልቡ እንዲህ እያለ ያስብ ነበር፤ “የዚያን የማይረባ ሰው ሀብት በዚህ በረሓ ለምን ስጠብቅ ቈየሁ? የእርሱ ከሆነው ንብረት ምንም ነገር ተሰርቆበት አያውቅም፤ ታዲያ እኔ ስላደረግሁለት መልካም ነገር እርሱ የሚከፍለኝ ወሮታ ይህ ሆኖ ቀረ!

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ዳዊ​ትም አለ፥ “ለዚህ ሰው ከሆ​ነው ሁሉ አንድ ነገር እን​ዳ​ይ​ጠ​ፋ​በት በእ​ው​ነት ከብ​ቱን ሁሉ በም​ድረ በዳ በከ​ንቱ ጠበ​ቅሁ፤ ከገ​ን​ዘቡ ሁሉ አን​ዳች ይወ​ስ​ዱ​በት ዘንድ ያዘ​ዝ​ነው የለም፤ እር​ሱም በበጎ ፋንታ ክፉ መለ​ሰ​ልኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ዳዊትም፦ ለዚህ ሰው ከሆነው ሁሉ አንድ ነገር እንዳይጠፋበት በእውነት ከብቱን ሁሉ በምድረ በዳ በከንቱ ጠበቅሁ፥ እርሱም ስለ በጎነቴ ክፋት መለሰልኝ።

Ver Capítulo Copiar




1 ሳሙኤል 25:21
19 Referencias Cruzadas  

ከከተማው ምንም ያህል ርቀው ሳይሄዱ፥ ዮሴፍ የቤቱን አዛዥ እንዲህ አለው፦ “እነዚያን ሰዎች ቶሎ ድረስባቸውና፥ ‘ለበጎ ነገር ስለምን ክፉ መለሳችሁ?


የአላዋቂና የነውረኞች ልጆች ናቸው፥ ከምድርም በግርፋት የተባረሩ ናቸው።”


በበጎ ፈንታ ክፋትን መለሱልኝ፥ ለብቻዬም ቀረሁ።


ከቁጣ ራቅ መዓትንም ተው፥ እንዳትበድል አትቅና።


ጠላቶቼ ሕያዋን ናቸው ይበረቱብኝማል፥ በጠማማነትም የሚጠሉኝ በዙ።


በመልካም ፋንታ ክፉን የሚመልስ፥ ክፉ ነገር ከቤቱ አትርቅም።


ለነፍሴ ጉድጓድ ቈፍረዋልና በውኑ በመልካም ፋንታ ክፉ ይመለሳልን? ስለ እነርሱ በመልካም ለመናገር ቁጣህንም ከእነርሱ ለመመለስ በፊትህ እንደ ቆምሁ አስታውስ።


ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ።


ተቆጡ፥ ኃጢአትን ግን አታድርጉ፤ በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፤


መራርነትና ንዴት ቁጣም፥ ጩኸትና ስድብን ሁሉ፥ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ።


ማንም ለሌላው በክፉ ፈንታ ክፉ እንዳይመልስ ተጠንቀቁ፤ ነገር ግን ሁልጊዜ እርስ በርሳችሁ እንዲሁም ለሁሉም መልካሙን ለማድረግ ትጉ።


የእግዚእብሔር ፈቃድ ከሆነ፥ ክፉ ሠርቶ መከራ ከመቀበል ይልቅ መልካም አድርጎ መከራ መቀበል ይሻላል።


ክፉን በክፉ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ፤ በዚህ ፈንታ ባርኩ፤ ምክንያቱም በረከትን ልትወርሱ ተጠርታችኋል።


ዳዊትም ሰዎቹን፥ “በሉ ሁላችሁም ሰይፋችሁን ታጠቁ” አላቸው። ስለዚህ ሁሉም ሰይፋቸውን ታጠቁ፤ ዳዊትም የራሱን ታጠቀ። አራት መቶ ያህል ሰዎች ከዳዊት ጋር ሲወጡ መቶ ያህሉ ግን ጓዝ ለመጠበቅ ቀሩ።


እነዚህ ሰዎች ግን እጅግ መልካም ነበሩ፤ ጉዳትም አላደረሱብንም፤ በዱር አብረናቸው በነበርንበት ጊዜም ሁሉ፥ ምንም ነገር አልጠፋብንም።


እርሷም በአህያዋ ላይ ተቀምጣ ወደ ሸለቆው በምትወርድበት ጊዜ ዳዊትና ሰዎቹ ወደ እርሷ ወረዱ፤ እርሷም አገኘቻቸው።


በዚህ ጊዜ በጎች እንደምትሸልት ሰምቻለሁ፤ እረኞችህ ከእኛ ጋር በነበሩበት ጊዜ፥ ያደረስንባቸው ጉዳት የለም፤ ቀርሜሎስ በነበሩበት ጊዜ ሁሉ፥ የጠፋባቸው አንዳች ነገር አልነበረም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos