ዘኍል 28:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም ወር በዓሥራ አምስተኛው ቀን በዓል ይሆናል፤ ሰባት ቀን እርሾ ያልነካው ቂጣ ይበላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚሁ ወር በዐሥራ ዐምስተኛው ቀን በዓል ይሆናል፤ እስከ ሰባትም ቀን ድረስ ቂጣ ብሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዐሥራ አምስተኛው ቀን በዓል ነው፤ ለሰባት ቀኖች መበላት ያለበት እርሾ ያልነካው ቂጣ ብቻ ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚህም ወር በዐሥራ አምስተኛው ቀን በዓል ይሆናል፤ ሰባት ቀን ቂጣ እንጀራ ትበላላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህም ወር በአሥራ አምስተኛው ቀን በዓል ይሆናል ሰባት ቀን ቂጣ እንጀራ ትበላላችሁ። |
የቂጣውን በዓል ጠብቅ፤ በተመደበው በአቢብ ወር ሰባት ቀን ያልቦካ ቂጣ እንዳዘዝሁህ ትበላለህ፤ በዚህ ወር ከግብጽ ምድር ወጥታችኋልና፥ በፊቴም ባዶ እጃችሁን አትታዩ።