ነህምያ 3:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሱ በኋላ የአካባቢው ሰዎች ካህናቱ አደሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከርሱም ቀጥሎ ያለውን ክፍል ከአካባቢው የመጡት ካህናት መልሰው ሠሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ቅጽር የሠሩ ካህናት ስም ዝርዝር ይህ ነው፦ በኢየሩሳሌም ዙሪያ የነበሩት ካህናት ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእርሱም በኋላ የአካባቢው ሰዎች ካህናቱ ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱም በኋላ የቈላው ሰዎች ካህናቱ አደሱ። |
ከእነርሱም በኋላ ብንያምና ሐሹብ ከቤታቸው ፊት ለፊት ያለውን አደሱ። ከእነርሱም በኋላ የአናንያ ልጅ የማዓሤያ ልጅ አዛርያ በቤቱ አጠገብ ያለውን አደሰ።