አምላክህ ጌታ እንድታደርግ የሚያዝህን ሁሉ አድርግ፤ በምትሄድበት ስፍራ ሁሉ የምታደርገው ማንኛውም ነገር እንዲከናወንልህ በሙሴ አማካይነት በተሰጠው ሕግ የተጻፉትን የእግዚአብሔርን ሕግና ትእዛዝ፥ ሥርዓትና ፈቃድ ሁሉ ጠብቅ፤
ነህምያ 1:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአንተ ላይ ታላቅ ክፋት ሠርተናል፤ ለአገልጋይህ ለሙሴ ያዘዝኸውን ሕጎች፥ ትእዛዛትና ፍርድ አልጠበቅንም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአንተ ላይ እጅግ ክፉ ሥራ ሠርተናል፤ ለባሪያህም ለሙሴ የሰጠኸውን ትእዛዝ፣ ሥርዐትና ሕግ አልጠበቅንም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአንተ ላይ በማመፅ ትእዛዞችህን ሁሉ ተላልፈናል፤ በአገልጋይህ በሙሴ አማካይነት የሰጠኸንንም ሕግና ሥርዓት አልጠበቅንም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኛም በአንተ ላይ እጅግ ክፉ ሠርተናል፤ ለባሪያህም ለሙሴ ያዘዝኸውን ትእዛዝና ሥርዐት፥ ሕጉንም አልጠበቅንም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኛም በአንተ ላይ እጅግ ክፉ ሠርተናል፤ ለባሪያህም ለሙሴ ያዘዝኸውን ትእዛዝና ሥርዓት ሕግም አልጠበቅንም። |
አምላክህ ጌታ እንድታደርግ የሚያዝህን ሁሉ አድርግ፤ በምትሄድበት ስፍራ ሁሉ የምታደርገው ማንኛውም ነገር እንዲከናወንልህ በሙሴ አማካይነት በተሰጠው ሕግ የተጻፉትን የእግዚአብሔርን ሕግና ትእዛዝ፥ ሥርዓትና ፈቃድ ሁሉ ጠብቅ፤
አሜስያስ የነፍሰ ገዳዮቹን ልጆች አልገደለም ነበር ምክንያቱም በሙሴ ሕግ መጽሐፍ እንደ ተጻፈ፥ ጌታ እንዲህ ብሎ አዝዞ ነበርና፦ “ሰው ሁሉ በገዛ ኃጢአቱ ይሙት እንጂ አባቶች በልጆች ፋንታ አይሙቱ፥ ልጆችም በአባቶች ፋንታ አይሙቱ።”
ይህ ዕዝራ ከባቢሎን መጣ፥ የእስራኤል አምላክ ጌታ ለሙሴ በሰጠው ሕግ ችሎታ ያለው ጸሐፊ ነበረ፤ የአምላኩ የጌታ እጅ በእርሱ ላይ ስለ ነበረች ንጉሡ የጠየቀውን ነገር ሁሉ ሰጠው።
እናንተ ኀጢአተኛ ሕዝብ፤ በደል የሞላበት ወገን፤ የክፉ አድራጊ ዘር፤ ምግባረ ብልሹ ልጆች ወዮላችሁ! ጌታን ትተዋል፤ የእስራኤልን ቅዱስ አቃለዋል፤ ጀርባቸውንም በእርሱ ላይ አዙረዋል።
እኔም አልኩ “በእርግጥ ትፈሪኛለሽ፥ እርማትንም ትቀበያለሽ፤ መኖሪያዋ አይጠፋም፥ ያቀድኩትም አይደርስም።” እነርሱ ግን በማለዳ ተነሥተው ድርጊታቸውን ሁሉ አረከሱ።
“አሁንም፥ እስራኤል ሆይ፥ እንድታደርጉአቸው በሕይወትም እንድትኖሩ፥ የአባቶቻችሁም አምላክ ጌታ ወደሚሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱ፥ የማስተምራችሁን ሥርዓትና ሕግጋት ስሙ።
ሙሴም እስራኤልን ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እስራኤል ሆይ፥ እንድትማሩአት በማድረግም እንድትጠብቁአት ዛሬ በጆሮአችሁ የምናገራትን ሕግና ሥርዓት ስሙ።