ዘሌዋውያን 26:40 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ነገር ግን እኔን በመቃወም ሄደዋልና፥ በእኔ ላይ ፈጽሞ በከዳተኝነት ያደረጉትን በደላቸውንና የአባቶቻቸውን በደል ይናዘዛሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ነገር ግን ለእኔ ያልታመኑበትንና በእኔም ላይ ያመፁበትን የራሳቸውን ኀጢአትና የአባቶቻቸውን ኀጢአት ቢናዘዙ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ነገር ግን የእናንተ ዘሮች የራሳቸውን ኃጢአት፥ እንዲሁም በእኔ ላይ ያመፁትንና የተቃወሙኝን የቀድሞ አባቶቻቸውን ኃጢአት ይናዘዛሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እንደ ከዱኝ፥ ቸልም እንዳሉኝ፥ በፊቴም አግድመው እንደ ሄዱ፥ ኀጢአታቸውንና፥ የአባቶቻቸውን ኀጢአት ይናዘዛሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእኔም ላይ በእንቢተኝነት ስለ ሄዱብኝ የበደሉኝን በደል፥ ኃጢአታቸውንም፥ የአባቶቻቸውንም ኃጢአት ይናዘዛሉ። |
ማርከው በወሰዱአቸው በጠላቶቻቸው አገር ሳሉ በፍጹም ልባቸው በእውነትና በቅን መንፈስ ተጸጽተው ንስሓ በመግባት አንተ ለቀድሞ አባቶቻችን ወደ ሰጠሃቸው ወደዚህች ምድር፥ አንተም ወደ መረጥኻት ወደዚህች ከተማና እኔ ለአንተ ወደ ሠራሁት ወደዚህ ቤተ መቅደስ ፊታቸውን መልሰው ቢጸልዩ፥
የእስራኤል አምላክ ጌታ ሆይ፥ አንተ ጻድቅ ነህ፥ እንደ ዛሬው እኛ አምልጠን ቀርተናል፥ እነሆ በፊትህ በበደላችን አለን፥ በዚህ ምክንያት በፊትህ ሊቆም የሚችል የለም።
እንዲህም አልሁ፦ “አምላኬ ሆይ፥ አፍሬአለሁ፤ አምላኬ ሆይ፥ ፊቴንም ወደ አንተ ለማንሣት እፈራለሁ፥ ኃጢአታችን ከራሳችን በላይ ከፍ ብሏልና፥ በደላችንም ወደ ሰማያት ወጥቷልና።
ሬስ። አቤቱ፥ ተጨንቄአለሁና፥ አንጀቴም ታውኮብኛልና ተመልከት፥ ዓመፃን ፈጽሞ አድርጌአለሁና ልቤ በውስጤ ተገላበጠብኝ፥ በሜዳ ሰይፍ ልጆቼን አጠፋ በቤትም ሞት አለ።
ኢያሱም አካንን እንዲህ አለው፦ “ልጄ ሆይ! ለእስራኤል አምላክ ለጌታ ክብር ስጥ፥ ለእርሱም ተናዘዝ፤ ያደረግኸውንም ንገረኝ፤ አትሸሽገኝ።”