ኢዮብ 6:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተስፋ የሌለው ሰው ንግግር እንደ ነፋስ ነውና ቃሌን ትገሥጹ ዘንድ ታስባላችሁን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም የተናገርሁትን ለማረም፣ ተስፋ የቈረጠውንም ሰው ቃል እንደ ነፋስ ለመቍጠር ታስባላችሁን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ የእኔን ንግግር እንደ ነፋስ ባዶ አድርጋችሁ ትቈጥሩታላችሁ፤ ታዲያ፥ ተስፋ ለቈረጥሁት ለእኔ መልስ መስጠት ለምን ትፈልጋላችሁ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የንግግራችሁም ማጽናናት ዕረፍትን አይሰጠኝም፤ የአንደበታችሁም ቅልጥፍና ደስ አያሰኘኝም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተስፋ የሌለው ሰው ንግግር እንደ ነፋስ ነውና ቃሌን ትገሥጹ ዘንድ ታስባላችሁን? |
እርሱ ግን፦ “አንቺ ከሰነፎች ሴቶች እንደ አንዲቱ ተናገርሽ፥ ከእግዚአብሔር እጅ መልካሙን ተቀበልን፥ ክፉ ነገርንስ አንቀበልምን?” አላት። በዚህ ሁሉ ኢዮብ በከንፈሩ አልበደለም።
ጌታም ይህንን ለኢዮብ ከተናገረ በኋላ፥ ቴማናዊውን ኤልፋዝን እንዲህ አለው፦ “እንደ አገልጋዬ እንደ ኢዮብ ቅንን ነገር ስለ እኔ አልተናገራችሁምና ቁጣዬ በአንተና በሁለቱ ባልንጀሮችህ ላይ ነድዶአል።
ከእንግዲህ እንደ ስሕተት ሽንገላ ባለ ተንኮል፥ በሰዎችም ማታለል ምክንያት፥ በነፈሰው የትምህርት ነፋስ ሁሉ እየተፍገመገምን፥ ወዲያና ወዲህም እየተንሳፈፍን፥ ሕፃናት መሆን አይገባንም።