ኢዮብ 38:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውኑ ለዝናብ አባት አለውን? ወይም የጠልን ነጠብጣብ የወለደ ማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዝናብ አባት አለውን? የጤዛን ጠብታ ማን ወለደው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዝናብንና ጤዛን የሚያስገኝ ማነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዝናብ አባቱ ማን ነው? ወይስ የጠልን ነጠብጣብ የወለደ ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በውኑ ለዝናብ አባት አለውን? ወይስ የጠልን ነጠብጣብ የወለደ ማን ነው? |
እናንተ የጊልቦዓ ተራሮች ሆይ፤ በዚያ የኀያሉ ሰው ጋሻ ረክሶአልና፤ የሳኦል ጋሻ በዘይት መወልወሉ ቀርቶአልና፤ ጠልም ሆነ ዝናብ አይውረድባችሁ፤ የቁርባን እህል የሚያበቅሉም እርሻዎች አይኑራችሁ።
በገለዓድ የምትገኘው የቱቢ ተወላጅ የሆነውና ኤልያስ ተብሎ የሚጠራው ነቢይ፤ ንጉሥ አክዓብን “በእኔ ቃል ካልሆነ በቀር በሚቀጥሉት ዓመቶች በምድር ላይ ጠል ወይም ዝናብ እንደማይኖር እኔ በማገለግለው በእስራኤል አምላክ፥ በሕያው ጌታ ስም እነግርሃለሁ” አለው።
ድምፁን ባሰማ ጊዜ ውኆች በሰማይ ይታወካሉ፥ ከምድርም ዳርቻ ደመናትን ከፍ ያደርጋል፤ ለዝናቡም መብረቅን ያደርጋል፥ ነፋስንም ከቤተ መዛግብቱ ያወጣል።
በውኑ በአሕዛብ ከንቱ ጣዖታት መካከል ዝናብን ሊያዘንብ የሚችል ይገኛልን? ወይስ ሰማይ ካፊያን መስጠት ይችላልን? አቤቱ አምላካችን ሆይ! አንተ አይደለህምን? አንተ እነዚህን ሁሉ ነገሮች አድርገሃልና ስለዚህ አንተን በተስፋ እንጠባበቃለን።
በልባቸውም፦ “የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ በጊዜው የሚሰጠውን፥ ለመከርም የተመደቡትን ወራት የሚጠብቅልንን አምላካችንን ጌታን እንፍራ” አላሉም።
እናንተ የጽዮን ልጆች፥ ጌታ አምላካችሁ ቀድሞ የሚደርሰውን ዝናብ ስለ ጽድቅ ሰጥቶአችኋልና፥ እንደ በፊትም ቀዳሚውንና የኋለኛውን ዝናብ አዝንቦላችኋልና በእርሱ ደስ ይበላችሁ፥ ለእርሱም እልል በሉ።
“እኔ ደግሞ መከር ሳይደርስ ገና ከሦስት ወር በፊት ዝናብ ከለከልኋችሁ፤ በአንድም ከተማ ላይ አዘነብሁ፥ በሌላውም ከተማ ላይ እንዳይዘንብ አደረግሁ፤ በአንድ ወገን ባለው መሬት ዘነበ፥ ባልዘነበበትም ወገን ያለው መሬት ደረቀ።
ይህን በማድረግ በሰማያት ላለው አባታችሁ ልጆች እንድትሆኑ ነው፤ እርሱ ለክፉዎችና ለደጎች ፀሐዩን ያወጣልና፥ ለጻድቃንና ለኃጥኣንም ዝናቡን ያዘንባልና።