ኢዮብ 30:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቆዳዬ ጠቈረ፥ ከእኔም ተለይቶ እርግፍግፍ አለ፥ አጥንቴም ከትኩሳት የተነሣ ተቃጠለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቈዳዬ ጠቍሮ ተቀረፈ፤ ዐጥንቴም በትኵሳት ነደደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቆዳዬ ጠቊሮ ተገለፈፈ፤ ሰውነቴም በትኩሳት ተቃጠለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቍርበቴ እጅግ ጠቈረ፥ አጥንቶቼም ከትኩሳት የተነሣ ተቃጠሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቁርበቴ ጠቈረ፥ ከእኔም ተለይቶ እርግፍግፍ አለ፥ አጥንቴም ከትኵሳት የተነሣ ተቃጠለች። |
ሔት። ፊታቸው ከጥቀርሻ ይልቅ ጠቁሮአል፥ በመንገድም አልታወቁም፥ ቁርበታቸው ወደ አጥንታቸው ተጣብቆአል፥ ደርቆአል፥ እንደ እንጨት ሆኖአል።
እኔ ሰምቻለሁ፥ አንጀቴ ራደብኝ፥ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፤ መበስበስ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ፥ በውስጤም ተንቀጠቀጥሁ፥ በአስጨነቁን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ፥ የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ።