ኢዮብ 29:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መንገዴ በቅቤ ይታጠብ በነበረ ጊዜ፥ ዓለቱ የዘይት ፈሳሽ ያፈስስልኝ በነበረ ጊዜ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መንገዴ በቅቤ የራሰ ነበር፤ ዐለቱም የወይራ ዘይት ያመነጭልኝ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግሮቼ እንኳ በወተት እስኪታጠቡ ድረስ ብዙ ወተት አገኝ ነበር። የወይራ ዛፎቼም በጭንጫ መሬት ላይ እንኳ ተተክለው እንደ ጐርፍ የሚወርድ ብዙ ዘይት ይሰጡኝ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቅቤ በመንገዴ ይፈስስ በነበረ ጊዜ፥ ወተት በተራራዬ ይፈስስልኝ በነበረ ጊዜ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንገዴ በቅቤ ይታጠብ በነበረ ጊዜ፥ ድንጋዩ የዘይት ፈሳሽ ያፈስስልኝ በነበረ ጊዜ። |
በወርቅና በብር አጌጥሽ፥ ልብስሽም ጥሩ በፍታ፥ ሐርና ወርቀዘቦ ነበር፥ የላመ ዱቄት፥ ማርና ዘይትም በላሽ፥ እጅግ በጣም ውብ ሆንሽ፥ ለንግሥትነትም በቃሽ።