ኢዮብ 15:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉ ሰው ዕድሜ ልኩን ሲሠቃይ ይኖራል፥ እንዲሁም ግፈኛ በተመደቡለት ዓመታት በሙሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉ ሰው ዕድሜውን ሙሉ፣ ጨካኙም በተመደበለት ዘመን ሁሉ ይሠቃያል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሰዎችን ሲጨቊን የኖረ ክፉ ሰው ዕድሜ ልኩን ሲሠቃይ ይኖራል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኃጥእ ሰው ዕድሜው በጭንቅ ያልፋል፥ ለግፈኛ የተመደቡ ዓመታቱም ሁሉ የተቈጠሩ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክፉ ሰው ዕድሜውን ሙሉ፥ ለግፈኛ በተመደቡለት በዓመታት ሁሉ በሕመም ይጣጣራል። |
ለሁሉም አንድ ዓይነት ዕጣ ክፍል መኖሩ ከፀሐይ በታች በሚደረገው ነገር በሙሉ ይህ ክፉ ነው፥ ደግሞም የሰው ልጆች ልብ በክፋት ተሞልታለች፥ በሕይወታቸውም ሳሉ እብደት በልባቸው ውስጥ ይኖራል፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሙታን ይወርዳሉ።