ኤርምያስ 4:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መከራ በመከራ ላይ ተጠርቶአል፤ ምድሪቱም ሁሉ ጠፍታለችና፤ በድንገትም ድንኳኔ በዐይን ቅጽበትም መጋረጃዎቼ ጠፉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጥፋት በጥፋት ላይ ይመጣል፤ ምድሪቱም በሞላ ባድማ ትሆናለች፤ ድንኳኔ በድንገት፣ መጠለያዬም በቅጽበት ጠፋ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መቅሠፍት በመቅሠፍት ላይ ይደራረባል፤ አገሪቱ በሙሉ ፈራርሳ ጠፍ ሆናለች፤ ድንኳኖቻችን በድንገት ወደሙ፤ መጋረጃዎቻቸውም በቅጽበት ተቀደዱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መከራ በመከራ ላይ ተጠርቶአል፤ ምድር ሁሉ ተዋርዳለችና፤ በድንገትም ድንኳኔ ጠፋ፤ መጋረጃዎችም ተቀዳደዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መከራ በመከራ ላይ ተጠርቶአል፥ ምድርም ሁሉ ተበዝብዛለችና፥ በድንገትም ድንኳኔ በቅጽበት ዓይንም መጋረጃዎቼ ጠፉ። |
ጌታም ሙሴን፦ “ለእስራኤል ልጆች ‘እናንተ አንገተ ደንዳና ሕዝብ ናችሁ፥ አንድ ጊዜ ከእናንተ ጋር ብወጣ አጠፋችኋለሁ፤ አሁንም በእናንተ ላይ የማደርገውን እንዳውቅ ጌጣችሁን አውጡ’ በላቸው አለው።”
ልቤ ስለ ሞዓብ አለቀሰ፤ ከእርሷ የሚሸሹ ወደ ዞዐር ወደ ዔግላት ሺሊሺያ ኮበለሉ፤ በሉሒት አቀበት ላይ እያለቀሱ ወጡ፤ በሖሮናይምም መንገድ የዋይታ ጩኽት አሰሙ።
የበዓላችንን ከተማ ጽዮንን ተመልከት፤ ዐይኖችህ የሰላም ማደሪያ፥ የማይወገድ ድንኳን፥ ካስማውም ለዘለዓለም የማይነቀል፥ አውታሩም ሁሉ የማይበጠስ የሆነውን ኢየሩሳሌምን ያያሉ።
አሁን ግን እነዚህ ሁለት ነገሮች፥ የወላድ መካንነትና መበለትነት፥ በአንድ ቀን በድንገት ይመጡብሻል፤ ምንም መተት ብታበዥና ምንም ዓይነት አስማት ቢኖርሽም ፈጽሞ አይቀሩልሽም።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በኢየሩሳሌም ላይ አራቱን ክፉ ፍርዶቼን ሰይፍ፥ ራብ፥ ክፉ አውሬና ቸነፈር፥ ሰውንና እንስሳን ከእርሷ ለማጥፋት ብሰድድም፥