ዋላ ደግሞ በምድረ በዳ ወለደች፥ ሣርም የለምና ግልገልዋን ተወች።
አንዳች ሣር ባለመኖሩ፣ የሜዳ አጋዘን እንኳ፣ እንደ ወለደች ግልገሏን ጥላ ትሄዳለች።
ሣር ካለመገኘቱ የተነሣ፥ አጋዘን እንደ ወለደች ግልገልዋን በሜዳ ላይ ጥላ ትሄዳለች።
ዋሊያዎች ደግሞ በምድረ በዳ ወለዱ፤ ሣርም የለምና ግልገሎቻቸውን ተዉ።
ንፍታሌም የተፈታ ሚዳቋ ነው፥ መልካም ቃልን ይሰጣል።
የጌታ ድምፅ ዋላዎችን ያጠነክራቸዋል፥ ጫካዎቹንም ይገልጣል፥ ሁሉም በመቅደሱ፦ ምስጋና ይላል።
የኔምሬም ውኆች ይደርቃሉ፤ ሣሩም ደርቋል፤ ለጋውም ጠውልጓል፤ ልምላሜውም ሁሉ የለም።
እንስሶች እጅግ ጮኹ፥ የላምም መንጎች ማሰማርያ የላቸውምና ተቅበዘበዙ፥ የበግም መንጎች እየተሰቃዩ ነው።